የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

ከአማራ ክልል በያዝነው ዓመት 170 ሺህ ኩንታል ጥራቱን የጠበቀ ቡና ለገበያ ለማቅረብ ታቅዷል

Oct 29, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

‎ባህርዳር ፤ ጥቅምት 18/2018(ኢዜአ)፦ከአማራ ክልል በያዝነው ዓመት 170 ሺህ ኩንታል ጥራቱን የጠበቀ ቡና ለገበያ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

‎በቢሮው የሆልቲካልቸር ባለሙያ አቶ አወቀ ዘላለም ለኢዜአ እንደገለፁት በክልሉ የቡና ልማትን በማስፋፋትና ምርታማነቱን በማሳደግ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየተሰራ ይገኛል።

‎‎በክልሉ በስነ ምህዳርና በአየር ንብረታቸው ተስማሚ በሆኑ አካባቢዎች በኩታ ገጠም ጭምር ከ34 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ የቡና ልማት እየተካሄደ መሆኑን ገልፀዋል።

‎ከዚህ ውስጥም ምርት መስጠት ከጀመረው 25 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ 170 ሺህ ኩንታል ጥራቱን የጠበቀ ቡና በማምረት ለአካባቢና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ የለቀማና ምርት ስብስባ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል።


‎አሁን ላይ ‎‎ለአምራች አርሶ አደሮች ስለቡና ምርት አሰባሰብ፣ አደራረቅና አዘገጃጀት ግንዛቤ በመፍጠር ጥራቱን የጠበቀ ቡና ለማቅረብ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

‎‎በምዕራብ ጎጃም ዞን የጃቢጠህናን ወረዳ ነዋሪ አርሶ አደር ውበት ተስፌ ግማሽ ሄክታር በሚጠጋ መሬታቸው ላይ የተሻሻለ ምርት የሚሰጥ የቡና ዝርያ እያለሙ መሆኑን ተናግረዋል።

‎ጥራቱን የጠበቀ ቡና ለገበያ ለማቅረብ ‎የደረሰውን ምርት እየለቀሙ በአልጋ ላይ በማድረቅ እያዘጋጁ መሆኑን ተናግረዋል።

‎‎የተሻሻለ የቡና ዝርያ በሩብ ሄክታር መሬታቸው ላይ በማልማት ተጠቃሚ መሆናቸውን የገለጹት ደግሞ በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የዳንግላ ዙሪያ ወረዳ ነዋሪ አርሶ አደር ሙላቱ እንግዳ ናቸው።


‎‎ዘንድሮ ወቅቱ ለቡና ልማት ተስማሚ በመሆኑ የተሻለ የቡና ምርት በመሰብሰብና በመሸጥ ከሰብል ልማቱ ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።

‎በክልሉ ባለፈው በጀት ዓመት 130 ሺህ ኩንታል ቡና ለገበያ መቅረቡን ከቢሮው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በከተሞቹ በትንሳዔ በዓል ገበያ በቂ ምርትና የእርድ እንስሳት ቀርቧል 

ሆሳዕና ፤ ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦በሆሳእና፣ ወላይታ ሶዶና ቦንጋ ከተሞች በትንሳዔ በዓል ገበያ በቂ የምርትና የእርድ እንስሳት አቅርቦት መኖሩ ተመለከተ። ...

Apr 12, 2026

የጉምሩክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የጉምሩክ አገልግሎት በሚያቀላጥፍ መልኩ እየተዘጋጀ ነው

አዲስ አበባ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦የጉምሩክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የጉምሩክ አገልግሎት በሚያቀላጥፍ መልኩ እየተዘጋጀ መሆኑን በሕ...

Apr 9, 2026

የማዕከል ወደ ሥራ መግባት በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀብት ወደ ላቀ የኢኮኖሚ ጥቅም ለመለወጥ ያስችላል

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፦ የአፋር ሰመራ ሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ወደ ሥራ መግባቱ በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀ...

Apr 1, 2026

<p>ተቋማት ራሳቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ ይገባል- ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...

Feb 28, 2025