🔇Unmute
ሮቤ፤ ጥቅምት 5/2018 (ኢዜአ):- የባህር በር ጥያቄው ኢትዮጵያ ከምትከተለው የፍትሃዊ ተጠቃሚነት እሳቤ የመነጨና የህልውና ጉዳይ በመሆኑ በሁሉም ዘንድ ሊደገፍ ይገባል ሲሉ የመደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ገለጹ።
የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የውሃ ኃብት አጠቃቀምና የሃይድሮሎጂ ረዳት ፕሮፌሰር አለማየሁ አባተ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት የጀመረችው ጥረት በቀጣናውና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተሰሚነቷን በተሻለ መልኩ የሚያሳድግ ሁሉን አቀፍ እንቅስቃሴ ነው።

ኢትዮጵያ የግዙፍ ኢኮኖሚና ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ባለቤት እንዲሁም ለቀይ ባህር በቅርብ ርቀት የምትገኝ መሆኗ ከሌሎች ወደብ አልባ አገራት ልዩ እንደሚያደርጋት የዓለም አቀፍ ተሞክሮን በማጣቀስ አብራርተዋል።
ኢትዮጵያ ዘላቂ የተፈጥሮ ሀብትን በፍትሃዊነት መጠቀም በሚለው እሳቤ የምታምንና እሳቤውንም በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ላይ በተግባር ማሳየቷን ጠቅሰዋል።
ይህም በመሆኑ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ከፍትሃዊ ተጠቃሚነት እሳቤ የሚመነጭና የህልውና ጉዳይ በመሆኑ በሁሉም ዘንድ ሊደገፍ ይገባል ሲሉ አስረድተዋል።
የባህር በር ጥያቄው ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ኢኮኖሚ መገንባት እንድትችል እና የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትልቅ ፋይዳ ያለው መሆኑንም ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ፍትሃዊ የባህር በር ጥያቄ የብሔራዊ ጥቅምና የህልውና ጉዳይ በመሆኑ ፍላጎቱን እውን ለማድረግ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ያሉት በዩኒቨርሲቲው የውኃና መስኖ የትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ አቶ ተስፋሁን አዲሱ ናቸው።

ኢትዮጵያ ባለፉት 30 ዓመታት ፍትሀዊ ባልሆነ መንገድ ወደብ አልባ መሆኗ የሚያስቆጭ መሆኑን ጠቅሰው ኢትዮጵያ የባሕር በር ስለሌላት ብቻ በዓለም አቀፍ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ የገቢና ወጪ የንግድ ሥርዓት ውስጥ ለከፍተኛ ወጪ ስትዳረግ መቆየቷን አስታውስዋል።
አሁን የጀመረችው ጥረት ከቀጣናው አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተሰሚነቷንና ተጽዕኖ ፈጣሪነቷን የሚያሳድግ በመሆኑ ጥያቄው በሁሉም ዘንድ ሊታገዝ ይገባል ብለዋል።
ሆሳዕና ፤ ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦በሆሳእና፣ ወላይታ ሶዶና ቦንጋ ከተሞች በትንሳዔ በዓል ገበያ በቂ የምርትና የእርድ እንስሳት አቅርቦት መኖሩ ተመለከተ። ...
Apr 12, 2026
አዲስ አበባ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦የጉምሩክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የጉምሩክ አገልግሎት በሚያቀላጥፍ መልኩ እየተዘጋጀ መሆኑን በሕ...
Apr 9, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፦ የአፋር ሰመራ ሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ወደ ሥራ መግባቱ በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025