🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 4/2018 (ኢዜአ)፡- መንግሥት የግብርና ኢንቨስትመንትን በማስፋፋት ለምግብ ዋስትና መረጋገጥና ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት የሚያበረክተው አስተዋፅኦ እንዲጨምር በፖሊሲ የተደገፈ ትኩረት መስጠቱን የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ ገለጹ፡፡
ግብርና በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ወሳኝ ሚና የሚጫወት ሲሆን፣ ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ከፍተኛውን ድርሻ ከመያዙም በላይ ለሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ለምግብ ዋስትና እና ለውጭ ምንዛሪ ገቢ ዋና ምንጭ ነው።
የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን እኖር ወረዳ በመገኘት፣ በግብርና ኢንቨስትመንት ተሰማርተው በሰብል፣ በአትክልት፣ በፍራፍሬ እና በቅመማ ቅመም ልማት የተሰማሩ የግል ባለሀብቶችን የሥራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል።

ሚኒስትሩ በሰጡት ማብራሪያ፤ በግብርና ኢንቨስትመንት የሚሰማሩ ባለሀብቶችን ተሳትፎ ለማበረታታት መንግሥት የተለያዩ የሕግ ማዕቀፎችን እና የድጋፍ ፓኬጆችን በማዘጋጀት እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል።
በሰብል ልማት ዘርፍ ብቻ ከ6 ሺህ በላይ ባለሀብቶች ወደ 2 ነጥብ 1 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ወስደው እየሠሩ መሆኑን ጠቁመው፤ ከዚህም ውስጥ 720 ሺህ ሄክታሩ ወደ ልማት ገብቷል ብለዋል።
ይህም በተለይ በቆላማ አካባቢዎች ታርሰው የማይታወቁ መሬቶች እንዲለሙ አስችሏል ነው ያሉት።
ኢትዮጵያ የግብርና እምቅ አቅሟን ተጠቅማ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በምታደርገው ጥረት የባለሀብቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን አብራርተዋል።
መንግሥት በሚቀጥሉት ጊዜያት ለግብርና ኢንቨስትመንት ሰፊ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሠራ ጠቁመው፣ አዲስ በወጣው የግብርናና የገጠር ልማት ፖሊሲ ከዋነኛ ምሰሶዎች መካከል አንዱ የግል ባለሀብቱን ተሳትፎ ማሳደግ መሆኑን ገልጸዋል።
የግብርና ልማት ግቦች የሆኑትን ምግብ ዋስትና ማረጋገጥ፣ አካታች የሥራ ዕድል መፍጠር፣ ለኢንዱስትሪ ግብዓት ማምረት፣ የኤክስፖርት ገቢን ማሳደግና ገቢ ምርቶችን መተካትን ለማሳካት የግል ባለሀብቶች ሚና ወሳኝ መሆኑን አስረድተዋል።
የባለሀብቶችን ተሳትፎ ለማጠናከርና የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶች በመለየት አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት ለስኬታማነታቸው ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንደሚደረግ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን በግብርና ኢንቨስትመንት ተሰማርተው የሚገኙት አቶ ዳኜ ዳባ በበኩላቸው፤ በሰብል፣ በቅመማ ቅመም፣ በአትክልት እና ፍራፍሬ ልማት ውጤታማ ሥራ እየሠሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር እንዲሁም ቀደም ሲል ከልማት ውጭ የነበረን መሬት ወደ ልማት በማስገባት ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ እያደረጉ መሆኑን ጠቁመዋል።
የግብርና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ የግብርና ምርቶችን ለውጭ ገበያ በማቅረብ፣ የምግብና ሥርዓተ ምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ብሎም ለሀገራዊ ምጣኔ ዕድገት ጉልህ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ ተገልጿል።
ሆሳዕና ፤ ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦በሆሳእና፣ ወላይታ ሶዶና ቦንጋ ከተሞች በትንሳዔ በዓል ገበያ በቂ የምርትና የእርድ እንስሳት አቅርቦት መኖሩ ተመለከተ። ...
Apr 12, 2026
አዲስ አበባ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦የጉምሩክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የጉምሩክ አገልግሎት በሚያቀላጥፍ መልኩ እየተዘጋጀ መሆኑን በሕ...
Apr 9, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፦ የአፋር ሰመራ ሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ወደ ሥራ መግባቱ በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025