🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ መስከረም 29/2018(ኢዜአ)፡-በስድስተኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር የህብረተሰቡን ንቃተ-ህሊና ማጎልበት የሚያስችሉ የንቅናቄ ተግባራት እንደሚከናወኑ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግሥት ሃሚድ ገለጹ፡፡
ስድስተኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር “የሳይበር ደህንነት-የዲጂታል ኢትዮጵያ መሰረት” በሚል መሪ ሀሳብ ከጥቅምት 1 እስከ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ይከበራል፡፡
ወሩን በማስመልከት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግሥት ሃሚድ በሰጡት መግለጫ፥ የሳይበር ጥቃት በዓለም አቀፍ ደረጃ በቁጥርም ሆነ በአይነት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል ብለዋል።
የሳይበር ደህንነት ወር መከበር ዋነኛ ዓላማው የዜጎችንና የተቋማትን የሳይበር ደህንነት ግንዛቤ የሚያጎለብቱ የንቅናቄ መድረኮችን በማዘጋጀት ሀገራዊ የሳይበር ደህንነት የመከላከል አቅምን ማሳደግ ነው።
የተቋማት አሰራር በስፋት ዲጂታላይዝ እየተደረገ በመሆኑ ከወዲሁ የሳይበር ደህንነት ዝግጁነታቸው እንዲጨምር የሚያስችሉ ስራዎች ይሰራሉ ብለዋል፡፡
የማህበረሰቡና የተቋማት የሳይበር ደህንነት ንቃተ-ህሊና አነስተኛ በመሆኑ መጠነ-ሰፊ ሃገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ንቃተ-ህሊና ማጎልበቻ ንቅናቄ እንደሚካሄድም ጠቁመዋል፡፡
“የሳይበር ደህንነት-የዲጂታል ኢትዮጵያ መሰረት” በሚል መሪ ሀሳብ የሚከበረው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር ሁለት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ትኩረት እንደሚያደርግም ተናግረዋል።
የመጀመሪያው የሃሰተኛ መረጃ ዝግጅት፣ ቁጥጥርና ስርጭትን ለመቆጣጠር እና ለመከላከል ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።
በሁለተኛ ደረጃ በዲጂታላይዜሽን ደህንነት ጉዞ የተቋማትን የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነት ለመቀነስ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።
የሳይበር ደህንነት ወር የመክፈቻ መርሃ ግብር ጥቅምት 1 ቀን 2018 እንደሚካሄድ ጠቅሰው ወሩን ሙሉ በተለያዩ ከተሞች የህብረተሰቡን ንቃተ ህሊና የሚያሳድጉ መርሃ ግብሮች እንደሚከናወኑ አስታውቀዋል።
ሆሳዕና ፤ ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦በሆሳእና፣ ወላይታ ሶዶና ቦንጋ ከተሞች በትንሳዔ በዓል ገበያ በቂ የምርትና የእርድ እንስሳት አቅርቦት መኖሩ ተመለከተ። ...
Apr 12, 2026
አዲስ አበባ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦የጉምሩክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የጉምሩክ አገልግሎት በሚያቀላጥፍ መልኩ እየተዘጋጀ መሆኑን በሕ...
Apr 9, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፦ የአፋር ሰመራ ሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ወደ ሥራ መግባቱ በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025