
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 12/2017(ኢዜአ)፦ የደንበኞች አገልግሎትን በማዘመን የኤሌክትሪክ መቆራረጥ ለመቀነስና ፍትሃዊ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገለጸ።
ተቋሙ አገልግሎቱን በማዘመን የኤሌክትሪክ መቆራረጥን ለመቀነስና ፍትሃዊ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ በሚያደርገው ጥረት ቅንጅታዊ አሰራር መፍጠር የሚያስችል የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ጉብኝትና የሚዲያ ፎረም አካሂዷል።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የፕሮሰስና ጥራት ማኔጅመንት ስራ አስፈፃሚ እሱባለው ጤናው እንደገለጹት፤ የኤሌክትሪክ መቆራረጥን ለማስቀረት በዋነኝነት መሰረተ ልማቶች ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ ነው።
ከተግባራቱ መካከል አገልግሎት አሰጣጡን በቴክኖሎጂ መደገፍ አንዱ መሆኑን አንስተው፤ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በዚህም ካሁን ቀደም በዘርፉ የነበሩ ተግዳሮቶች እየተሻሻሉ መምጣታቸውን ጠቁመዋል፡፡
የኤሌክትሪክ መቆራረጥን ለማስቀረት የተጀመረው ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረገ አሰራር ማህበረሰቡ እንዲያውቀው ለማድረግና ብልሹ አሰራሮችን ለማጋለጥ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ሚና የላቀ ነው ብለዋል።
የአገልግሎቱ የኮሙኒኬሽን ዘርፍ ስራ አስፈፃሚ አንዋር አብራር በበኩላቸው፤ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማትን ከስርቆት ለመጠበቅ የማህበረሰቡ ተሳትፎ እንደሚያስፈልግ አንስተዋል።
መገናኛ ብዙሃንም በማህበረሰቡ ዘንድ ግንዛቤ ከመፍጠር አኳያ የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ነው የተናገሩት፡፡
ለዚህም አገልግሎቱ ከመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ጋር ተቀራርቦ መስራት የሚያስችለውን ጉብኝት ማድረግና የሚድያ ፎረም ማቋቋም ማስፈለጉን ጠቅሰዋል።
ሆሳዕና ፤ ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦በሆሳእና፣ ወላይታ ሶዶና ቦንጋ ከተሞች በትንሳዔ በዓል ገበያ በቂ የምርትና የእርድ እንስሳት አቅርቦት መኖሩ ተመለከተ። ...
Apr 12, 2026
አዲስ አበባ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦የጉምሩክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የጉምሩክ አገልግሎት በሚያቀላጥፍ መልኩ እየተዘጋጀ መሆኑን በሕ...
Apr 9, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፦ የአፋር ሰመራ ሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ወደ ሥራ መግባቱ በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025