
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 5/2017(ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትን ለማጠናከር የበኩሉን ሚና እየተወጣ እንደሚገኝ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የትምህርትና ቋንቋዎች ጥናት ኮሌጅ "ጥራት ያለው ትምህርት ለኢትዮጵያ ዘላቂ ልማት" በሚል መሪ ሃሳብ የትምህርት ጥራትና ፍትሃዊነትን በሚመለከት ውይይት ተካሂዷል፡፡
ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የ2030 ዘላቂ የልማት አጀንዳ አካል የሆነውን የትምህርት ጥራትና ፍትሃዊነትን የማረጋገጥ ግብን ለማሳካት በርካታ ተግባራትን ማከናወኗ በመድረኩ ተገልጿል፡፡
ከዚህ አኳያ ያስመዘገበቻቸውን ስኬቶች ለማስቀጠልና የገጠሙ ተግዳሮቶችን በመፍታት ግቡን ሙሉ በሙሉ ለማሳካት በሚቻልበት ሁኔታ ዙሪያ ምክክር ተደርጓል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) እንደገለጹት፥ ዩኒቨርሲቲው ለዘላቂ የልማት ግቦች ስኬት የሚጠበቅበትን እያበረከተ ነው፡፡
በዚህም ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምሮችን እንዲሁም የፈጠራ ሥራና የማህበረሰብ አገልግሎት በማከናወን ለግቡ ስኬት የበኩሉን እየተወጣ መሆኑን ተናግረዋል።
ዩኒቨርሲቲው ግቦቹን በስትራቴጂክ ዕቅዱ በማካተት ለስኬቱ እየሰራ እንደሚገኝ ጠቅሰው፥ ዘላቂ የልማት ግቦችን ውጤታማ ለማድረግ የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንት ጀይሉ ኡመር (ዶ/ር) በበኩላቸው ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለዘላቂ የልማት ግቦች ስኬት ትልቅ ሚና እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡
ለዚህም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥና ተደራሽነትን በማስፋት ለግቡ ስኬት ወሳኝ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
በዩኒቨርሲቲው የትምህርትና ቋንቋዎች ጥናት ኮሌጅ ኤክስኪዩቲቭ ዲን የቆየዓለም ደሴ (ዶ/ር) ፥ የትምህርትን ዘላቂ የልማት ግብ ለማሳካት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚና፣ ትምህርትን በፋይናንስ መደገፍና ወቅታዊ አተገባበርን በተመለከተ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት እንደተካሄደባቸው ገልጸዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ለዘላቂ የልማት ግቡ ስኬት የተለያዩ ጥናትና ምርምሮችን በማካሄድ ላይ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡
ሆሳዕና ፤ ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦በሆሳእና፣ ወላይታ ሶዶና ቦንጋ ከተሞች በትንሳዔ በዓል ገበያ በቂ የምርትና የእርድ እንስሳት አቅርቦት መኖሩ ተመለከተ። ...
Apr 12, 2026
አዲስ አበባ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦የጉምሩክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የጉምሩክ አገልግሎት በሚያቀላጥፍ መልኩ እየተዘጋጀ መሆኑን በሕ...
Apr 9, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፦ የአፋር ሰመራ ሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ወደ ሥራ መግባቱ በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025