
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 5/2017(ኢዜአ)፦ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ለማሳያነት ያስገነባው 100 ኪሎ ዋት የሚያመነጭ የሶላር ፕሮጀክት ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ(ዶ/ር) የሶላር ፕሮጀክቱን መርቀው ስራ አስጀምረዋል።
ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት በአገሪቱ ኢነርጂን ለማስፋፋት በተሰሩ ስራዎች በአገሪቱ የሀይል አቅርቦትን በማስፋፋት በርካታ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል።
በሚኒስቴሩ ግቢ ውስጥ የተገነባው የሶላር ኢነርጂ በከተማ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚቻል ማሳያ ነው ብለዋል።
ሶላር ኢነርጂው የተቋሙን ሀይል ከመሸፈን በተጨማሪ ወደ ዋና ግሬድ በመግባት ለሌሎች ሀይል መስጠት የሚችል መሆኑን ተናግረዋል።
የተመረቀው የሶላር ኢነርጂ ባለሀብቶች የራሳቸውን ሀይል አመንጭተው እንዲጠቀሙ ምሳሌ የሚሆን ፕሮጀክት መሆኑን አስታውቀዋል።
ሆሳዕና ፤ ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦በሆሳእና፣ ወላይታ ሶዶና ቦንጋ ከተሞች በትንሳዔ በዓል ገበያ በቂ የምርትና የእርድ እንስሳት አቅርቦት መኖሩ ተመለከተ። ...
Apr 12, 2026
አዲስ አበባ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦የጉምሩክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የጉምሩክ አገልግሎት በሚያቀላጥፍ መልኩ እየተዘጋጀ መሆኑን በሕ...
Apr 9, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፦ የአፋር ሰመራ ሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ወደ ሥራ መግባቱ በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025