
አዲስ አበባ፤ሰኔ 3/2017(ኢዜአ)፦በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ስራዎች የሚያስደንቁ መሆናቸውን የአርሜንያ ሪፐብሊክ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቫሃን ኮስታኒያን ገለጹ፡፡
ኢትዮጵያ እና አርመኒያ ያላቸው የረጅም ጊዜ ግንኙነትን ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችሉ ተግባራት እንደሚከናወኑም ገልጸዋል።
የአርሜንያ ሪፐብሊክ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቫሃን ኮስታኒያን ዛሬ ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡
ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቫሃን ኮስታኒያን እንደገለጹት፤ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የተመለከቷቸው ትልልቅ የልማት ስራዎችና ግንባታዎች የሚስደንቁና የከተማዋን ዓለምአቀፍ ተወዳዳሪነት የሚያሳድጉ ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ ሰው ወዳድ፣ እንግዳ ተቀባይ ነው ያሉት ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኮስታኒያን፤ በኢትዮጵያ ቆይታቸው መልካም ጊዜ ማሳለፋቸውን ገልጸዋል፡፡
አርመኒያ ትምህርት፣ቴክኖሎጂ እና ጤና ከፍተኛ እውቅና ያገኘችባቸው ዘርፎች መሆናቸውን ጠቁመው፤ በእነኚህ እና በሌሎችም ዘርፎች ያላትን ልምድ ለኢትዮጵያ ለማካፈል ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል፡፡
በሌላ መልኩም በዲጂታላይዜሽን እና የመንግስት አገልግሎትን በቴክኖሎጂ ከመደገፍ አኳያም ከኢትዮጵያ ጋር በጋራ ለመሥራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ እና አርመኒያ የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናክር እንደሚሰሩም ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቫሃን ኮስታኒያን ተናግረዋል፡፡
አርመኒያ ከኢትዮጵያ ጋራ ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን ጠቁመው፤ በኢትዮጵያ በኩልም ይህንን ቁርጠኝነት መመልከታቸውን ጠቁመዋል፡፡
ሆሳዕና ፤ ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦በሆሳእና፣ ወላይታ ሶዶና ቦንጋ ከተሞች በትንሳዔ በዓል ገበያ በቂ የምርትና የእርድ እንስሳት አቅርቦት መኖሩ ተመለከተ። ...
Apr 12, 2026
አዲስ አበባ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦የጉምሩክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የጉምሩክ አገልግሎት በሚያቀላጥፍ መልኩ እየተዘጋጀ መሆኑን በሕ...
Apr 9, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፦ የአፋር ሰመራ ሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ወደ ሥራ መግባቱ በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025