
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 27/2017(ኢዜአ)፦ የጎንደር ከተማ ወደ ሠላም መመለሷ በርካታ ልማቶች በስኬት እንዲከናወኑ ማስቻሉን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ተናገሩ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በጎንደር ከተማ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
በጉብኝታቸውም ከአኩሪ አተር የምግብ ዘይት የሚያመርት ፋብሪካን መርቀው ሥራ ያስጀመሩ ሲሆን፤ በክልል ደረጃ በጎንደር ከተማ የተዘጋጀውን የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ የቀረቡ ምርቶችንም ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
በጎንደር ከተማ የኮሪደር ልማት እንዲሁም የአጼ ፋሲል ቤተ-መንግሥት እድሳትንም ጎብኝተዋል።

ጉብኝቱን አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፤ ጎንደር ከተማ ተከስቶ ከነበረው የጸጥታ ችግር በመውጣት ትልልቅ የልማት ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን ተመልክተናል ብለዋል።
በኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖም በምግብ ማቀነባበር መስክ የተሰማሩ፣ በጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ከሀገር አልፎ ለውጭ ገበያ መቅረብ የሚችሉ ምርቶችን መመልከታቸውን ገልጸው፤ በዚህም ትልቅ አቅም እየተፈጠረ መሆኑን ተገንዝበናል ነው ያሉት።
በሌማት ትሩፋት መርሃ ግብርም ውጤታማ እንቅስቃሴ መኖሩን የሚያመላክቱ ስኬቶችን አይተናል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህም ሠላም በመስፈኑ የተገኘ ውጤት ነው ብለዋል።

በኮሪደር ልማትም በጎንደር ከተማ ኀብረተሰቡን በማሳተፍ የተከናወኑ ተግባራት በአርአያነት የሚወሰዱ መሆናቸውን አንስተዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በከተማዋ የኮሪደር ልማቱ በጥሩ የአፈጻጸም ደረጃ ላይ መሆኑንም እንዲሁ።

የፋሲል ቤተ-መንግሥት እድሳት ለጎንደር ከተማ ኮሪደር ልማት ትልቅ መነቃቃት መፍጠሩንም አብራርተዋል።
የቤተ መንግሥቱ እድሳት የቅርሱን ይዘት እንደጠበቀ በመከናወን ላይ እንደሚገኝ ጠቅሰው ይህም ለሌሎች ግንባታዎች ምሳሌ የሚሆን ውጤት የተገኘበት ነው ብለዋል።
ሆሳዕና ፤ ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦በሆሳእና፣ ወላይታ ሶዶና ቦንጋ ከተሞች በትንሳዔ በዓል ገበያ በቂ የምርትና የእርድ እንስሳት አቅርቦት መኖሩ ተመለከተ። ...
Apr 12, 2026
አዲስ አበባ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦የጉምሩክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የጉምሩክ አገልግሎት በሚያቀላጥፍ መልኩ እየተዘጋጀ መሆኑን በሕ...
Apr 9, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፦ የአፋር ሰመራ ሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ወደ ሥራ መግባቱ በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025