
ሰቆጣ፤ግንቦት 16/2017 (ኢዜአ) ፦የመኸር ወቅት የሰብል ልማት ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችሉ የዝግጅት ስራዎችን እያከናወኑ እንደሚገኙ በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የጋዝጊብላ ወረዳ አርሶ አደሮች ገለፁ።
በብሔረሰብ አስተዳደሩ በ2017/18 የመኸር ወቅት 120 ሺህ 638 ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን ታቅዶ እየተሰራ መሆኑ ተመላክቷል።
በጋዝጊብላ ወረዳ የመስቀሎ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አርሶ አደር ፋንታው ምርኩዜ ለኢዜአ እንደገለፁት፥በመኸር ወቅቱ የስንዴ፤የገብስና የጤፍ ሰብሎችን ለማልማት አቅደው ዝግጅት እያደረጉ ይገኛሉ።
ከዚህ ውስጥም አንድ ሄክታር የእርሻ መሬትን በስንዴ ሰብል ለመሸፈን አቅደው ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል።
ለዚህም አንደኛ ዙር እርሻ በማረስ ዝግጅት ማድረጋቸውን ጠቅሰው፥ የአፈር ማዳበሪያ በመጠቀም የዘር ስራውን ለማከናወን መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።
አርሶ አደር ባየ አበራ በበኩላቸው፥ግማሽ ሄክታር መሬት የስንዴ ሰብልን ጨምሮ ሌሎች ሰብሎችን ለማልማት የእርሻ ዝግጅት እያካሄዱ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ስንዴን ከአካባቢው አርሶ አደሮች ጋር በመሆን በኩታ ገጠም ለመዝራት ዝግጅት እያደረጉ ሲሆን ለመኸር እርሻው የሚሆን ማዳበሪያ ከወዲሁ መቅረቡን ገልፀዋል።
በዚህም መሬቱን ደጋግሞ በማረስና በቂ ግብዓት በመጠቀም ምርታማነትን በሚያሳድግ አግባብ የሰብል ልማት ስራውን እያከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል።
በብሔረሰብ አስተዳደሩ በ2017/18 የመኸር ወቅት 120 ሺህ 638 ሄክታር መሬትን በተለያዩ ሰብሎች በዘር ለመሸፈን ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን የገለፁት ደግሞ የአስተዳደሩ የግብርና መምሪያ ሃላፊ አቶ አዲስ ወልዴ ናቸው።
የመኸር ሰብል ልማቱን ምርታማነት ለማሳደግም 32 ሺህ ኩንታል ማዳበሪያ ቀርቦ 12 ሺህ ያህሉ ለአርሶ አደሮች መሰራጨቱን ተናግረዋል።
በአስተዳደሩ የአካባቢን ፀጋ በመለየት ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው፥ በመኸር ወቅት እርሻው መታረስ ከሚችለው መሬት 110 ሺህ ሄክታር ያህሉ መሬት አንድ ዙር ታርሶ ለዘር ዝግጅት መደረጉን ገልፀዋል።
በብሔረሰብ አስተዳደሩ በ2017/18 የመኸር ወቅት ከሚለማው መሬት 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
ሆሳዕና ፤ ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦በሆሳእና፣ ወላይታ ሶዶና ቦንጋ ከተሞች በትንሳዔ በዓል ገበያ በቂ የምርትና የእርድ እንስሳት አቅርቦት መኖሩ ተመለከተ። ...
Apr 12, 2026
አዲስ አበባ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦የጉምሩክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የጉምሩክ አገልግሎት በሚያቀላጥፍ መልኩ እየተዘጋጀ መሆኑን በሕ...
Apr 9, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፦ የአፋር ሰመራ ሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ወደ ሥራ መግባቱ በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025