
ቦንጋ፤ ግንቦት 12/2017(ኢዜአ)፦ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በገቡት ውል መሰረት የወርቅ ምርትን ለማዕከላዊ ገበያ በማያቀርቡ አምራቾችና አቅራቢዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰዱን የክልሉ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ኤጀንሲ አስታወቀ።
በበጀት ዓመቱ ባለፉት አስር ወራት ከ124 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ከክልሉ ለብሔራዊ ባንክ መቅረቡም ተጠቁሟል።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ገብረማሪያም ሰጠኝ፣ በክልሉ በርካታ የከበሩና ከፊል የከበሩ እንዲሁም ለግንባታ የሚያገለግሉ ማዕድናት እንዳሉ ገልጸው፣ ከእነዚህ መካከል ወርቅና የድንጋይ ከሰል በሰፊው እየተመረቱ ይገኛሉ ብለዋል።
በወርቅ ማምረት ሂደት ሥራ ፍቃድ ወስደው ወደ ሥራ የገቡ 85 የወርቅ አምራች ማህበራት እንዳሉም ጠቅሰዋል።
ከእነዚህ ማህበራት መካከል አብዛኞቹ በገቡት ውል መሠረት አምርተው ለገበያ አለማቅረባቸው ለብሔራዊ ባንክ የሚቀርብ የወርቅ ምርት አፈጻጸም እንዲያንስ ማድረጉንም አንስተዋል።
ችግሩን ለመፍታት በማህበራቱ ላይ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ገልጸው፣ ለአብነትም ለ36 ወርቅ አምራችና አቅራቢዎች የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱን ጠቅሰዋል።
በተጨማሪም ለ24 ወርቅ አምራቾች ከባድ ማስጠንቀቂያ እንዲሁም የሰባት አምራች ማህበራት ፈቃድ እንዲሰረዝ ተደርጓል ብለዋል።
በቀሪ ወራት የተጠናከረ የድጋፍና ክትትል ሥራ በመስራት አፈጻጸሙን ለማሻሻል እንደሚሰራ አቶ ገብረማሪያም ገልጸዋል።
ማህበራቱ በተለይም የአካባቢ ጥበቃና ማህበራዊ ደህንነት ህግን አክብረው መልሶ የማልማት ሥራ እንዲሰሩ በተቀናጀ መልኩ ክትትልና ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑንም አስታውቀዋል።
ሆሳዕና ፤ ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦በሆሳእና፣ ወላይታ ሶዶና ቦንጋ ከተሞች በትንሳዔ በዓል ገበያ በቂ የምርትና የእርድ እንስሳት አቅርቦት መኖሩ ተመለከተ። ...
Apr 12, 2026
አዲስ አበባ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦የጉምሩክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የጉምሩክ አገልግሎት በሚያቀላጥፍ መልኩ እየተዘጋጀ መሆኑን በሕ...
Apr 9, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፦ የአፋር ሰመራ ሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ወደ ሥራ መግባቱ በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025