አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 29/2017 (ኢዜአ)፦በአጀንዳ 2063 የበለጸገች አፍሪካ እውን ለማድረግ የተያዘውን ግብ ለማሳካት የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የበለጠ ማሳደግ እንደሚገባ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ መንበር አምባሳደር ሳልማ ማሊካ ገለጹ።
ስድስተኛው የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ሴት ስራ ፈጣሪዎች የንግድ ትርዒትና ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ ተከፍቷል።
በንግድ ትርዒቱ ላይ ከሃያ አንዱ የኮሜሳ አባል አገራት የተወጣጡ ከ200 በላይ ሴት ስራ ፈጣሪዎች ምርትና አገልግሎታቸውን አቅርበዋል።
በንግድ ትርዒቱ መክፈቻ የተገኙት የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ መንበር አምባሳደር ሳልማ ማሊካ እንደገለጹት፤ በአፍሪካውያን መካከል የሚደረገውን የንግድ ልውውጥ በማሳደግ የአህጉሪቷን የኢኮኖሚ ውህደት ማፋጠን ይገባል።
የአፍሪካ ህብረት የሴቶችን እኩልነት ለማረጋገጥና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ቀርፆ ተግባራዊ እያደረገ መሆኑንም ነው ያነሱት።
ሴቶችን ያሳተፈ አህጉራዊ ውህደት ውጤታማ መሆኑ አያጠራጥርም ያሉት አምባሳደር ሳልማ ማሊካ፤ የበለፀገች አፍሪካን እውን ለማድረግ የኮሜሳ አባል አገሮች የበለጠ ተቀናጅተው ሊሰሩ እንደሚገባም አመልክተዋል።
የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ ኮሜሳ ሴት ነጋዴዎች ፌዴሬሽን ሊቀ መንበር ማውረን ሱምብዌ የሴቶችን እኩልነት ማረጋገጥ የመብት ጥበቃ ብቻ ሳይሆን ልማትንም ማፋጠን ነው ብለዋል።
የአፍሪካ አጀንዳ 2063 እውን የሚሆነው ለሴቶች ምቹ ከባቢ በመፍጠርና የኢኮኖሚ አቅማቸውን በማጠናከር ነው ብለዋል።
በተለያዩ የሥራ መስኮች የተሰማሩ ሴት ሥራ ፈጣሪዎችን ማበረታታትና ዕኩል ዕድል መስጠት ለአገር ምጣኔ ሀብት ዕድገት የማይተካ ሚና እንዳለውም አንስተዋል።
የኮሜሳ አባል አገራት ሴት ሥራ ፈጣሪዎችን የሚያበረታቱ ፖሊሲዎችን መቅረፅና ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸውም ተናግረዋል።
የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ (ኮሜሳ) ዋና ፀኃፊ ቺሌሴ ካፕዌ የኮሜሳን አባል አገራት የንግድ ትስስር የበለጠ በማጠናከር ሰፊ ቁጥር ያለውን ህዝብ ተጠቃሚ ማድረግ ይገባል።
ሴቶችና ወጣቶች ለአገር ዕድገት ያላቸውን ጉልህ ሚና የበለጠ ለማሳደግ የሚያጋጥማቸውን ተግዳሮቶች በጋራ መፍታት ያስፈልጋል ነው ያሉት።
የንግድ ትርዒቱ ሴት ሥራ ፈጣሪዎች እርስ በእርሳቸው የልምድ ልውውጥ እንዲያደርጉና የገበያ ትስስር እንዲፈጥሩ ዕድል ይፈጥራል ብለዋል።
#Ethiopian_News_Agency
#ኢዜአ
#Ethiopiaየበለጸገች አፍሪካን እውን ለማድረግ የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የበለጠ ማሳደግ ይገባል -የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀመንበር አምባሳደር ሳልማ ማሊካ

#Ethiopia
ሆሳዕና ፤ ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦በሆሳእና፣ ወላይታ ሶዶና ቦንጋ ከተሞች በትንሳዔ በዓል ገበያ በቂ የምርትና የእርድ እንስሳት አቅርቦት መኖሩ ተመለከተ። ...
Apr 12, 2026
አዲስ አበባ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦የጉምሩክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የጉምሩክ አገልግሎት በሚያቀላጥፍ መልኩ እየተዘጋጀ መሆኑን በሕ...
Apr 9, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፦ የአፋር ሰመራ ሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ወደ ሥራ መግባቱ በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025