የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ከ110 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ማድረጉን ገለጸ

May 7, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 28/2017(ኢዜአ)፡- የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ከ110 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ማድረጉን አስታወቀ።

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለኢዜአ በላከው መረጃ እንዳስታወቀው፤ በተከናወነው የመረጃ ስምሪትና ኦፕሬሽን በአፋር ክልል ገቢረሱ ዞን አሚባራ ወረዳ ብርጌድ በተባለ አካባቢ ግምታቸው ከ110 ሚሊዮን ብር በላይ የሆኑ መድኃኒቶች፣ ሺሻዎች፣ ሲጋራዎች፣ ልባሽ እና አዳዲስ ልብሶች በቁጥጥር ሥር ውለው በአዋሽ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ገቢ እንዲሆኑ ተደርጓል ብሏል።

በተወሰደው ኦፕሬሽን የመከላከያ ሠራዊት፣ የፌደራል ፖሊስ እና የአፋር ክልል ፖሊስ አባላት በቅንጅት መሥራታቸውንም አገልግሎቱ አስታውቋል።


የአገልግሎት መሥሪያ ቤቱ መረጃ እንዳመላከተው፤ በቁጥጥር ስር የዋሉት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው ቢሰራጩ በኢኮኖሚ እና በሕዝብ ጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትሉ ከመሆናቸውም በላይ አጠቃላይ የንግድ ስርዓቱን ሊያዛቡ የሚችሉ መሆናቸውን አመላክቷል፡፡

በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ የሚፈፀሙ አሻጥሮችን፣ ሕገ-ወጥ እንቅስቃሴዎችንና ወንጀሎችን እየተከታተለ አስፈላጊው እርምጃ እንዲወሰድ እያደረገ መሆኑንም ጠቁሟል።


በቀጣይም በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ አሻጥሮችን በሚፈፅሙ ማናቸውም አካላት ላይ የሚደረገው ክትትልና የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡

ሕገ-ወጥ እንቅስቃሴዎችን በመከታተልና መረጃ በመስጠት ረገድ የአካባቢው ማኅበረሰብ ያደረገው አስተዋፅዖ ከፍተኛ መሆኑንም ገልጿል።

የሀገርን ደኅንነት አደጋ ላይ ከሚጥሉ፣ የኅብረተሰቡን ጤና ከሚጎዱና ኢኮኖሚውን ከሚያቃውሱ ሕገ-ወጥ እንቅስቃሴዎች ጋር በተያያዘ መረጃ ያላቸው ዜጎች ለጸጥታና ደኅንነት አካላት ጥቆማ በመስጠት ሀገራዊ ግዴታቸውን እንዲወጡ ጥሪ መቅረቡንም አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ በላከው መረጃ ጥሪ አቅርቧል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በከተሞቹ በትንሳዔ በዓል ገበያ በቂ ምርትና የእርድ እንስሳት ቀርቧል 

ሆሳዕና ፤ ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦በሆሳእና፣ ወላይታ ሶዶና ቦንጋ ከተሞች በትንሳዔ በዓል ገበያ በቂ የምርትና የእርድ እንስሳት አቅርቦት መኖሩ ተመለከተ። ...

Apr 12, 2026

የጉምሩክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የጉምሩክ አገልግሎት በሚያቀላጥፍ መልኩ እየተዘጋጀ ነው

አዲስ አበባ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦የጉምሩክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የጉምሩክ አገልግሎት በሚያቀላጥፍ መልኩ እየተዘጋጀ መሆኑን በሕ...

Apr 9, 2026

የማዕከል ወደ ሥራ መግባት በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀብት ወደ ላቀ የኢኮኖሚ ጥቅም ለመለወጥ ያስችላል

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፦ የአፋር ሰመራ ሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ወደ ሥራ መግባቱ በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀ...

Apr 1, 2026

<p>ተቋማት ራሳቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ ይገባል- ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...

Feb 28, 2025