
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 17/2017(ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች ዜጎችን ተጠቃሚ ከማድረግ ባሻገር የመዲናዋን የዲፕሎማሲ ከተማነት የሚያጠናክሩ መሆናቸውን የተቋማት የስራ ኃላፊዎች ገለፁ።
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስተባባሪነት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና የማህበራዊ ዘርፍ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
ከጎበኟቸው የልማት ስራዎች መካከል በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ሰሞኑን የተመረቀው የካዛንቺስ የኮሪደር ልማትን ጨምሮ የአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል፣ የእንስሳት ልማትና ልህቀት ማዕከል፣ የገላን ጉራ የተቀናጀ የመኖሪያና የልማት መንደር እንዲሁም የጫካ ፕሮጀክት ይገኙበታል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ የማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወርቀሰሙ ማሞ በዚሁ ጊዜ ለኢዜአ እንዳሉት በከተማዋ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች ሁሉን አቀፍ ናቸው ብለዋል።
ልማቶቹ ዜጎችን በጤና፣ በባህልና ስፖርት እንዲሁም በማህበራዊ ዘርፍ ተጠቃሚ የሚያደርጉ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በተጨማሪም የከተማዋን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ለማሳደግ እየተከናወኑ የሚገኙ ሁሉን አቀፍ የልማት ስራዎችን በተግባር መመልከታቸውን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍፁም አረጋ በበኩላቸው አዲስ አበባ ተጨባጭና ዘርፈ ብዙ የልማት ተግባራትን እያከናወነች ተገኛለች ብለዋል።
የልማት ስራዎቹ ዜጎችን ተጠቃሚ ከማድረግ ባለፈ የሀገርን ገፅታ የሚገነቡ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው እንዳሉት አዲስ አበባ የአፍሪካ መዲናነቷን የሚያረጋግጥ የልማት ስራ እያከናወነች ነው።
መዲናዋ በርካታ ዓለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ መድረኮችን የምታዘጋጅ እንዲሁም የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት መቀመጫ መሆኗን አውስተው ይህን በሚመጥን ልክ የልማት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን መገንዘባቸውን ገልጸዋል።

በዚህም አዲስ አበባ ለነዋሪዎቿ ብቻ ሳይሆን ለምታስተናግዳቸው እንግዶችም ምቹ እና ተመራጭ የማድረግ ስራው አበረታች ነው ብለዋል።
የልማት ስራዎቹ ባህልን፣ ስፖርትንና ኪነጥበብን ሊያሳድጉ የሚችሉ መሰረተ ልማቶችን ያካተቱ እንደሆኑ መመልከታቸውን ጠቅሰው፤ ይህም ዘርፎቹን ማሳደግ የሚያስችሉ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ ሀይማኖት አለማየሁ ናቸው።
ሆሳዕና ፤ ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦በሆሳእና፣ ወላይታ ሶዶና ቦንጋ ከተሞች በትንሳዔ በዓል ገበያ በቂ የምርትና የእርድ እንስሳት አቅርቦት መኖሩ ተመለከተ። ...
Apr 12, 2026
አዲስ አበባ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦የጉምሩክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የጉምሩክ አገልግሎት በሚያቀላጥፍ መልኩ እየተዘጋጀ መሆኑን በሕ...
Apr 9, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፦ የአፋር ሰመራ ሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ወደ ሥራ መግባቱ በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025