የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

ከአነስተኛ ኢንዱስትሪዎች ወደ ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች መስፈንጠር እንደሚቻል ከቬይትናም ተሞክሮ መቅሰም ተችሏል

Apr 21, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 11/2017(ኢዜአ)፦ ከአነስተኛ ኢንዱስትሪዎች ወደ ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች መስፈንጠር እንደሚቻል ከቬይትናም ተሞክሮ መቅሰም መቻሉን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍስሃ ይታገሱ(ዶ/ር) ገለጹ።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍስሃ ይታገሱ(ዶ/ር) የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የቬይትናም ቆይታን አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም ቬይትናም በጥቂት ዓመታት ውስጥ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ከፍተኛ እመርታን ካስመዘገቡ ሀገራት መካከል አንዷ ናት ብለዋል፡፡

በተለይም የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን በመሳብ አማራጭ የኢንቨስትመንት ማዕከል በመሆን ትልቅ ዕድገት ማስመዝገቧን ጠቁመው፤ በዚህም የአምራች ዘርፉ በኢኮኖሚው ውስጥ ያለው ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

ከቬይትናም በአጭር ጊዜ ውስጥ ኢንዱስትራላይዜሽንን ለማስፋት የሄዱበት መንገድ በተሞክሮነት የሚወሰድ መሆኑን ተናግረዋል።

በተለይም በዓለም አቀፍ የማኑፋክቸሪንግ እሴት ሰንሰለት ውስጥ የሚኖር ጂኦፖለቲካዊ አካሄዶችን በማየት የወሰዱት እርምጃ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት መሳቡንና ይህም ትልቅ ትምህርት የተወሰደበት መሆኑን አንስተዋል።

ትልቅ ትምህርት የተወሰደበት ዓለም አቀፍ ሁኔታዎችንና አዝማሚያዎችን በመተንተን ኢንዱስትሪዎች ወደ ሀገር እንዲመጡ መሳብ መሆኑን ገልጸው፤ ይህም ቬይትናምን የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የስበት ማዕከል እንድትሆን አስችሏታል ብለዋል።

እንዲሁም ከትንንሽ ኢንዱስትሪዎች ወደ ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች መስፈንጠር እንደሚቻልም ከቬትናም ተሞክሮ መቅሰም መቻሉን ገልጸዋል።

ኢንዱስትሪዎች በሀገር ውስጥ ግብዓት እንዲጠቀሙ ክትትል እና ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባም ነው ዶክተር ፍሰሃ ያብራሩት።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በከተሞቹ በትንሳዔ በዓል ገበያ በቂ ምርትና የእርድ እንስሳት ቀርቧል 

ሆሳዕና ፤ ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦በሆሳእና፣ ወላይታ ሶዶና ቦንጋ ከተሞች በትንሳዔ በዓል ገበያ በቂ የምርትና የእርድ እንስሳት አቅርቦት መኖሩ ተመለከተ። ...

Apr 12, 2026

የጉምሩክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የጉምሩክ አገልግሎት በሚያቀላጥፍ መልኩ እየተዘጋጀ ነው

አዲስ አበባ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦የጉምሩክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የጉምሩክ አገልግሎት በሚያቀላጥፍ መልኩ እየተዘጋጀ መሆኑን በሕ...

Apr 9, 2026

የማዕከል ወደ ሥራ መግባት በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀብት ወደ ላቀ የኢኮኖሚ ጥቅም ለመለወጥ ያስችላል

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፦ የአፋር ሰመራ ሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ወደ ሥራ መግባቱ በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀ...

Apr 1, 2026

<p>ተቋማት ራሳቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ ይገባል- ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...

Feb 28, 2025