
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 9/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን እምቅ የልማት ጸጋዎች በማስተዋወቅ የኢንቨስትመንት ፍሰትን ማሳደግ እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አስገነዘቡ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ባለፉት የለውጥ ዓመታት የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት ምህዳር ለማሻሻል ያከናወናቸውን ተግባራትና አገልገሎት አሰጣጡን በዋና መስሪያ ቤቱ ተገኝተው ተመልክተዋል።
በጉብኝታቸውም ኮሚሽኑ በርካታ የሪፎርም ተግባራትን ማከናወኑን መመልከታቸውን ገልጸዋል።

ተቋሙ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ እና ዘመናዊ የዲጂታል አሰራሮችን የተከተለ የደንበኞች አገልግሎትን ተግባራዊ አድርጎ እየሰራ እንደሚገኝም ተጠቅሷል።
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ለዘርፉ ትልቅ ዕድል የከፈተ ሲሆን በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን በመሳብ ረገድ የተገኘው ስኬት ይህንኑ የሚያሳይ ነው ብለዋል።
በቀጣይ ኮሚሽኑ የጀመረውን አበረታች እና ከኢኮኖሚ ዕቅዶች ጋር የተጣጣሙ ዒላማ ተኮር የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማስተዋወቅ የኢንቨስትመንት ፍሰትን ማሳደግ ላይ በትኩረት እንዲሰራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን(ዶ/ር) የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጉብኝት በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ፥ ኮሚሽኑ ምቹ የሥራ ከባቢና ቀልጣፋ የአገልግሎት አሰጣጥ መዘርጋቱን አንስተዋል።
ኮሚሽኑ በተጨባጭ አስደናቂ የለውጥ ሥራዎችን ማከናወኑን በተግባር በማየታቸው መደሰታቸውን እንደገለጹም ነው ኮሚሽነሩ የጠቀሱት።
በቀጣይም ኮሚሽኑ የተሻለች ሀገር በመገንባት ሂደት ጉልህ አበርክቶውን አጠናክሮ እንዲቀጥል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሥራ መመሪያ መስጠታቸውንም ገልጸዋል።
ሆሳዕና ፤ ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦በሆሳእና፣ ወላይታ ሶዶና ቦንጋ ከተሞች በትንሳዔ በዓል ገበያ በቂ የምርትና የእርድ እንስሳት አቅርቦት መኖሩ ተመለከተ። ...
Apr 12, 2026
አዲስ አበባ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦የጉምሩክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የጉምሩክ አገልግሎት በሚያቀላጥፍ መልኩ እየተዘጋጀ መሆኑን በሕ...
Apr 9, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፦ የአፋር ሰመራ ሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ወደ ሥራ መግባቱ በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025