
አዳማ፤ ሚያዚያ 9/2017(ኢዜአ)፦ በአዳማ ከተማ ለበዓል የምርት አቅርቦትና የእርድ እንስሳት በተለያዩ የገበያ አማራጮች በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረበ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ንግድ ፅህፈት ቤት አስታወቀ።

የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ጢሎ ዱግዳ፤ ለበዓል የሚያስፈልጉ የግብርና እና ኢንዱስትሪ ምርቶች እንዲሁም የእርድ እንስሳት በብዛትና በጥራት መቅረቡን ገልጸዋል።
ለምርቱ አቅርቦት ከባለድርሻ አካላትና አርሶ አደሮች ጋር በመተባበር ከተለያዩ አካባቢዎች የገቡ ሲሆን በከተማዋ የተለያዩ የገበያ አማራጮች በተመጣጣኝ ዋጋ ቀርቧል ብለዋል።

በከተማዋ 28 የእሁድ ገበያዎችና ሌሎች ኢንተርፕራይዞች ባቋቋማቸው የገበያ ማእከላት ምርቶች በብዛትና በጥራት መቅረባቸውንም አንስተዋል።
የበዓል ግብይቱን በተመለከተ በሁሉም አካባቢዎች ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን አንስተው ህገ ወጥ እንቅስቃሴ በሚያደርጉ ላይ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑንም ተናግረዋል።

የአዳማ ኢንቨስትምነት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ብዙነህ ግርማ፤ ለበዓሉ አስፈላጊ የሆኑ ምርቶች በብዙ አማራጭ በተመጣጣኝ ዋጋ መቅረባቸውን ገልጸዋል።
ለበዓሉ ለሽያጭ የተዘጋጁ ከ10ሺህ በላይ ዶሮዎች፣ እንቁላል፣ ወተትና ሌሎችም ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ስለመዘጋጀቱ ጠቁመዋል።

የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት አባል ከሆኑት መካከል ወጣት ናኔሶ ፍታላ፤ በዓሉን አስመልክቶ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን ጨምሮ ሌሎችም በብዛትና በጥራት ለሸማቾች መቅረባቸውን ተናግሯል።

ከአዳማ ከተማ ነዋሪዎች መካከል ወይዘሮ መስከረም ጣፋ፤ አቅርቦቱ ሁሉም በየአቅሙ የሚሸምትበት አማራጭ መኖሩን ተናግረዋል።
ሆሳዕና ፤ ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦በሆሳእና፣ ወላይታ ሶዶና ቦንጋ ከተሞች በትንሳዔ በዓል ገበያ በቂ የምርትና የእርድ እንስሳት አቅርቦት መኖሩ ተመለከተ። ...
Apr 12, 2026
አዲስ አበባ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦የጉምሩክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የጉምሩክ አገልግሎት በሚያቀላጥፍ መልኩ እየተዘጋጀ መሆኑን በሕ...
Apr 9, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፦ የአፋር ሰመራ ሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ወደ ሥራ መግባቱ በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025