
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 9/2017(ኢዜአ)፦በሸገር ከተማ ለፊታችን የትንሳዔ በዓል ታስበው በተመቻቹ የገበያ አማራጮች ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እያገኙ መሆናቸውን ሸማቾች ገለጹ።
በከተማው በሁሉም ክፍለ ከተሞች የትንሳዔ በዓልን አስመልክቶ የፍጆታ ምርቶች አቅርቦትን ለማሳደግ የሚያስችሉ ባዛርና የእሁድ ገበያዎች መመቻቸታቸውም ተገልጿል።
አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ ሸማቾች እንዳሉት፥ ለበዓሉ ተብለው በተለያዩ አካባቢዎች በተከፈቱ ባዛሮችና ገበያዎች የበዓል ፍጆታዎችን በዓይነትና በተመጣጠኝ ዋጋ እያገኙ መሆናቸውን ተናግራል።
ከሸማቾቹ መካከል አቶ ባይሳ አራርሳ ለበዓሉ አስፈላጊ የሆኑት ምርቶች በአንድ ማዕከል ላይ የተገኙ ሲሆን ከወጪና ድካምም ታድጎናል ብለዋል።
በባዛሩ በቂ ምርት መቅረቡን ጠቅሰው፥ ጥራት ያለው ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ እያገኘን ነው ብለዋል።
ባዛሩና የቅዳሜ ገበያው ለአምራቹ የገበያ ትስስር ለመፍጠር እንዳገዘ የገለጹት አቶ ባይሳ፤ አቅርቦቱ ገበያን ከማረጋጋት አንጻር ከፍተኛ ሚና እንዳለውም ተናግረዋል።
ከአሁን በፊት በዓል ሲደርስ ምርት በመደበቅና ዋጋን በመጨመር ማህበረሰቡ ሲማረር እንደነበረ አስታውሰው፥የዘንድሮው ግን ካለፈው አንጸር የተሻለ ለውጥ እንዳለውና በተቀናጀ መልኩ ክትትልና ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን መታዘባቸውንም ተናግረዋል።
ሌላዋ ሸማች ወይዘሮ ዓለምቱ አበራ በበኩላቸው፥ በባዛሩ የቀረቡ ምርቶች ከሌሎች ቦታዎች አንጻር በእያንዳንዱ ምርት ላይ ከ5- እስከ 10 ብር የዋጋ ቅናሽ ለውጥ መኖሩን ተናግረዋል።
ለዘንድሮ የትንሳዔ በዓል የምንፈልጋቸውን ምርቶች በአንድ ማዕከል በተመጣጣኝ ዋጋ እያገኘን ስለሆነ በጣም ደስተኛ ነን ብለዋል።
ወጣት ጥሩነሽ አበቡ በበኩሏ፥ መንግስት ባመቻቸለቸው ምቹ ሁኔታ ተደራጅተው ያመረቱትን ምርት ለበዓል ገበያ ማቅረባቸውን ተናግራለች።
ምርቱ በብዛት እየቀረበ መሆኑን ገልጻ፥ያመረትነውን ምርት ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ገበያን ከማረጋጋት አንጻር የድርሻችንን እየተወጣን ነው ብላለች።
ለበዓሉ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርትን በማቅረብ በተመጣጣኝ ዋጋ እየሸጡ መሆናቸውን የተናገሩት ደግሞ፤ አቶ ኬይሩን መሃመድ ናቸው።
ግብይቱ በደማቅ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን ጠቅሰው ሸማቹም በምርታችንና በዋጋችን ደስተኛ ነው ብለዋል።
ለበዓሉ የእንስሳት ተዋጽኦ በባዘሩ ያቀረቡት ወይዘሮ ሰናይት በላይ በበኩላቸው፥ ጥራት ያለው ምርት ማቅረባቸውን ተናግረዋል።
ዋጋውም የህብረተሰቡን አቅም ባገናዘበ መልኩ ስለሆነ ህዝቡን ተጠቃሚ እያደረጉና በጥሩ ሁሄታ በደስታ ምርቱን እየሸጡ መሆኑን ተናግረዋል።
ሆሳዕና ፤ ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦በሆሳእና፣ ወላይታ ሶዶና ቦንጋ ከተሞች በትንሳዔ በዓል ገበያ በቂ የምርትና የእርድ እንስሳት አቅርቦት መኖሩ ተመለከተ። ...
Apr 12, 2026
አዲስ አበባ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦የጉምሩክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የጉምሩክ አገልግሎት በሚያቀላጥፍ መልኩ እየተዘጋጀ መሆኑን በሕ...
Apr 9, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፦ የአፋር ሰመራ ሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ወደ ሥራ መግባቱ በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025