
አዲስ አበባ፤ሚያዚያ 4/2017 (ኢዜአ) ፦የህብረት ስራ ዩኒየኖች የአፈር ማዳበሪያ በወቅቱ ለተጠቃሚው አርሶ አደር ተደራሽ እንዲሆን ለማድረግ በትኩረት መስራት እንዳለባቸው የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ሶፊያ ካሳ (ዶ/ር) አሳሰቡ።
ሶፊያ ካሳ (ዶ/ር)፥ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ቢሾፍቱ አካባቢ ለውጭ ገበያ የሚቀርብ በ78 ሄክታር መሬት ላይ በግል ባለሃብት እየለማ የሚገኝ ሹገር ስናብ እና ማንጄቱት የተሰኙ የአትክልት ማሳዎችን ጎብኝተዋል።
በተጨማሪም በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ በማዕከላዊ መጋዘንና በመሰረታዊ የገበሬዎች የህብረት ስራ ዩኒየኖች በኩል ያለውን የምርት ዘመን የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦትና ስርጭት ሂደት ተመልክተዋል።
ሚኒስትር ዴኤታዋ በአፈር ማዳበሪያ ስርጭት ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ማስተካከል እንደሚገባ ገልጸዋል።
ማዳበሪያውን በወቅቱ ለተጠቃሚው አርሶ አደር ተደራሽ እንዲሆን የህብረት ስራ ዩኒየኖች በትኩረት እንዲሰሩ ማሳሰባቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።
ሆሳዕና ፤ ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦በሆሳእና፣ ወላይታ ሶዶና ቦንጋ ከተሞች በትንሳዔ በዓል ገበያ በቂ የምርትና የእርድ እንስሳት አቅርቦት መኖሩ ተመለከተ። ...
Apr 12, 2026
አዲስ አበባ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦የጉምሩክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የጉምሩክ አገልግሎት በሚያቀላጥፍ መልኩ እየተዘጋጀ መሆኑን በሕ...
Apr 9, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፦ የአፋር ሰመራ ሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ወደ ሥራ መግባቱ በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025