
መጋቢት 27/2017(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተከናወኑ የልማት ስራዎች ብልጽግናን ለማረጋገጥ መሰረት የጣሉ መሆናቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀይሉ አዱኛ ገለጹ።
በኦሮሞ ባህል ማዕከል ላለፉት ሶስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የክልሉ መንግስትን የለውጥ ዓመታት ጉዞ የሚያሳይ አውደ ርዕይ ዛሬ ተጠናቋል።

በአውደ ርዕይው መዝጊያ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀይሉ አዱኛ፤ በክልሉ ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተከናወኑ የልማት ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ ናቸው ብለዋል።
በለውጡ ዓመታት የተከናወኑ የልማት ስራዎች ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገትን እውን ለማድረግና ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ የሚያግዙ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
በአጠቃላይ በክልሉ በለውጡ ዓመታት የተከናወኑ የልማት ስራዎች የብልጽግና ጉዞን ለማረጋገጥ መሰረት የጣሉ ናቸው ብለዋል።
ለሶስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው አውደ ርዕይም በክልሉ የተመዘገቡ የልማት ድሎች የታዩበት እና ክልሉ ያለውን እምቅ አቅም ማስተዋወቅ የተቻለበት መሆኑንም አብራርተዋል።
አውደ ርዕዩ በክልሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች መካከል መረጃ የመያዝ፣ የማከማቸት፣ የመጠበቅ እንዲሁም የማሳየት ልምድ ልውውጥ የተደረገበት መሆኑንም ጠቁመዋል።
ይህም የዲጂታል ጉዞን እውን ለማድረግ ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸው ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል።
በአውደ ርዕዩ ላይ የተሳተፉትን እና ለስኬታማነቱ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
ሆሳዕና ፤ ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦በሆሳእና፣ ወላይታ ሶዶና ቦንጋ ከተሞች በትንሳዔ በዓል ገበያ በቂ የምርትና የእርድ እንስሳት አቅርቦት መኖሩ ተመለከተ። ...
Apr 12, 2026
አዲስ አበባ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦የጉምሩክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የጉምሩክ አገልግሎት በሚያቀላጥፍ መልኩ እየተዘጋጀ መሆኑን በሕ...
Apr 9, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፦ የአፋር ሰመራ ሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ወደ ሥራ መግባቱ በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025