
ባህር ዳር መጋቢት 24/2017 በአማራ ክልል እየተከናወነ ያለው የህብረት ስራ ማህበራት የሪፎርም ስራ ተጨባጭ ውጤቶችን እያስገኘ መሆኑን የክልሉ ህብረት ስራ ማህበራት ማስፋፊያ ባለስልጣን አስታወቀ።
የባለስልጣኑ ያለፉት ስምንት ወራት ዕቅድ አፈፃፀምና የተከናወኑ የሪፎርም ተግባራት ግምገማ በባህር ዳር ከተማ ዛሬ ተካሂዷል።

የባለስልጣኑ ኃላፊ አቶ ጌትነት አማረ እንደገለፁት፤ ህብረት ስራ ማህበራት ውጤታማ ተግባራትን ማከናወን እንዲችሉ የሚያግዝ ሪፎርም እየተካሄደ ይገኛል።
በዚህም ባለፈው አንድ ዓመት ተግባራዊ የተደረገው የሪፎርም አተገባበር ውጤት እያስገኘ መሆኑን ተናግረዋል።
በተካሄደው የሪፎርም ስራም የህብረት ስራ ማህበራትን ደረጃ የመለየትና መረጃ የማደራጀት ውጤታማ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሆነ ገልፀዋል።
ቀደም ሲል በስም ብቻ ተደራጅተው የነበሩ 901 የህብረት ስራ ማህበራት ባለፈው አንድ ዓመት 603ቱ በአዲስ መልክ እንዲደራጁ መድረጉን አመልክተዋል።
እንዲሁም ቀደም ሲል ስድስት የነበሩ ዩኒኖችን ወደ ሦስት እንዲዋሃዱ በማድረግ በፋይናንስና በሰው ኃይል ረገድ ጠንካራ እንዲሆኑ መደረጉን ገልፀዋል።

የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አጀበ ስንሻው፤ ህብረት ስራ ማህበራቱ ለኢኮኖሚ ዕድገቱ የማይተካ ሚናቸውን እየተጫወቱ ይገኛል ብለዋል።
የተጀመረው ማህበራቱ ሪፎርም የማድረግ ተግባር ጠንካራ የህብረት ስራ ማህበራት እንዲገነቡ እያስቻለ ነው ብለዋል።
የባለስልጣኑ የህብረት ስራ ማህበራት ማደራጃ ዳይሬክተር ቄስ እሽቱ መብራት በበኩላቸው፤ በክልሉ የተደራጁ ከ29 ሺህ የሚበልጡ የህብረት ስራ ማህበራት እንደሚገኙም ገልፀዋል።
ማህበራቱም ከ6 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ አባላት እንዳላቸው ጠቅሰው፤ በሪፎርሙ ጠንክረው እንዲወጡና ህብረተሰቡን ተጠቃሚ እንዲያደርጉ እየተሰራ ነው ብለዋል።
''ሪፎርሙ ተግባራዊ መደረጉ ህብረት ስራ ማህበራት ጠንክረው እንዲወጡ ዕድል ፈጥሯል'' ያሉት ደግሞ የደቡብ ወሎ ዞን ህብረት ስራ ማህበራት ማስፋፊያ ተጠሪ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ እሽትዬ ገበያው ናቸው።
ይህም አባል ማህበራት እንዲጠናከሩ በማድረግ አባላት ተጠቃሚ እንዲሆኑና ብቃት ባላቸው አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲመሩ ዕድል መፍጠሩ ውጤታማ ስራ እንዲያከናውኑ አስችሏል።
መድረኩ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን የክልል፣ የዞንና የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች፣ ዩኒየኖችና ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛል።
ሆሳዕና ፤ ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦በሆሳእና፣ ወላይታ ሶዶና ቦንጋ ከተሞች በትንሳዔ በዓል ገበያ በቂ የምርትና የእርድ እንስሳት አቅርቦት መኖሩ ተመለከተ። ...
Apr 12, 2026
አዲስ አበባ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦የጉምሩክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የጉምሩክ አገልግሎት በሚያቀላጥፍ መልኩ እየተዘጋጀ መሆኑን በሕ...
Apr 9, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፦ የአፋር ሰመራ ሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ወደ ሥራ መግባቱ በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025