
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 11/2017 (ኢዜአ)፦ በሪፎርም ስራው የኢንዱስትሪው የማምረት አቅም ወደ 61 በመቶ ማደጉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፥ መንግስት የኢንዱስትሪውን ዘርፍ በአጠቃላይ ኢኮኖሚ ውስጥ ያለውን ድርሻ ለማሳደግ እያከናወነ ባለው ስራ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል።
ሪፎርሙ ሲጀመር 47 በመቶ የነበረው የማምረት አቅም በዘንድሮው ዓመት ወደ 61 በመቶ ማደጉን እና ይህም ትልቅ እምርታ እንደሆነ ተናግረዋል።
በተያዘው ዓመት ከ55 በላይ አዳዲስ ፋብሪካዎች ወደ ስራ መግባታቸውን ገልጸዋል።
በምግብ ማቀነባበሪያ፣ በጨርቃ ጨር እና በተለያዩ ዘርፎች እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች ተዳምረው የኢንዱስትሪው ዘርፍ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘግባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።
ሆሳዕና ፤ ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦በሆሳእና፣ ወላይታ ሶዶና ቦንጋ ከተሞች በትንሳዔ በዓል ገበያ በቂ የምርትና የእርድ እንስሳት አቅርቦት መኖሩ ተመለከተ። ...
Apr 12, 2026
አዲስ አበባ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦የጉምሩክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የጉምሩክ አገልግሎት በሚያቀላጥፍ መልኩ እየተዘጋጀ መሆኑን በሕ...
Apr 9, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፦ የአፋር ሰመራ ሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ወደ ሥራ መግባቱ በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025