
አዲስ አበባ፤መጋቢት 8/2017 (ኢዜአ ):-የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ሶስተኛውን ቀጣናዊ የውሃ ፎረም ከግንቦት 11 እስከ 13 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ያካሂዳል።
“ለዘላቂ ቀጣናዊ የከርሰምድር ውሃ ሀብት ትብብር የሚሆን የአሰራር ማዕቀፍ መፍጠር” የፎረሙ መሪ ሀሳብ ነው።
ፎረሙ ቀጣናዊ የከርሰምድር የውሃ ሀብት ትብብርን ማጠናከር ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑን ኢጋድ ለኢዜአ በላከው መረጃ አመልክቷል።
የከርሰምድር ውሃ ሀብት ለውሃ ደህንነት፣ኢኮኖሚ ልማት እና ለከባቢ አየር መረጋጋት ቁልፍ ሚና እንዳለው ቀጣናዊ ተቋሙ ገልጿል።
በከፍተኛ ቁጥር እየጨመረ የመጣው የህዝብ እድገት፣የክትመት መስፋፋት፣ተለዋዋጭ የአየር ንብረት እና የውሃ ፍላጎት መጨመር የዘላቂ የከርሰምድር ውሃ አጠቃቀምን ከመቼውም ጊዜ በላይ አስፈላጊነቱ እንዲጨምር ማድረጉን አስታውቋል።
ለዚህም የተቀናጀ አስተዳደር እና የፖሊሲ ልማት ቁልፍ መሆኑ ተመላክቷል።
በዚህ ረገድ ሶስተኛው የኢጋድ ፎረም ለድንበር ተሻጋሪ የከርሰምድር ውሃ ሀብት አስተዳደር ቋሚ ማዕቀፍ ለመቅረፅ መልካም አጋጣሚን እንደሚፈጥር ነው ኢጋድ በመረጃው ያመለከተው።
ፎረሙ በዘርፉ ባሉ ጥናት እና ምርምሮች ዙሪያ የእውቀት ልውውጥ ለማድረግ እንዲሁም በኢጋድ አባል ሀገራት፣ የልማት አጋሮች እና ዓለም አቀፍ ተቋማት መካከል ያለውን አጋርነት የማጠናከር ውጥን ይዟል።
የከርሰምድር የውሃ ሀብት መረጃ በበቂ ሁኔታ በሌለባቸው ቀጣናዎች ላይ ፈጠራ እና አዲስ የአሰራር ዘዴን የተከተሉ ግምገማ ማድረግ እንዲሁም የማይበገር የከርሰምድር ውሃ ሀብት ትብብር መፍጠር የሚያስችል ረቂቅ ፍኖተ ካርታ ማዘጋጀት ሌሎች የፎረሙ አጀንዳዎች ናቸው።
በፎረሙ ላይ ፖሊሲ አውጪዎች፣ ተመራማሪዎች፣ የውሃ ዘርፍ ባለሙያዎች፣ የልማት አጋሮች እና ዓለም አቀፍ ባለድርሻ አካላት እንደሚሳተፉ ኢጋድ በመረጃው ላይ አመልክቷል።
ሁለተኛው የኢጋድ የውሃ ፎረም እ.አ.አ በ2022 በዩጋንዳ ኢንቴቤ መካሄዱ የሚታወስ ነው።
ሆሳዕና ፤ ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦በሆሳእና፣ ወላይታ ሶዶና ቦንጋ ከተሞች በትንሳዔ በዓል ገበያ በቂ የምርትና የእርድ እንስሳት አቅርቦት መኖሩ ተመለከተ። ...
Apr 12, 2026
አዲስ አበባ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦የጉምሩክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የጉምሩክ አገልግሎት በሚያቀላጥፍ መልኩ እየተዘጋጀ መሆኑን በሕ...
Apr 9, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፦ የአፋር ሰመራ ሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ወደ ሥራ መግባቱ በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025