
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 4/2017(ኢዜአ)፦ ለዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ቁልፍ ሚና ያላቸውን የቴክኖሎጂና የፈጠራ ሃሳቦችን ማጎልበት የሚያስችል ምቹ ምህዳር መፈጠሩን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለፀ።
የአፍሪካ ሮቦቲክስ ሻምፒዮንሽፕ 2025 ውድድር በሳይንስ ሙዚየም ተጀምሯል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ባይሳ በዳዳ(ዶ/ር) እንዳሉት፤ በዚህ ዘመን እንደ ሮቦቲክስ እና ሰው ሰራሽ አስተውሎት ያሉ ቴክኖሎጂዎች ለሀገራት እጅግ አስፈላጊ ናቸው።
ኢትዮጵያ ዘላቂና ቀጣይነት ያለው ዕድገት ለማስመዝገብ እንዲሁም ቀጣይነት ያለው ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት እየሰራች ነው ብለዋል።
የተለያዩ የህግ ማዕቀፎችን በማዘጋጀት በዲጂታል ዘርፍ ምቹ ምህዳር ለመፍጠር መሰራቱን አንስተው ይህም በዘርፉ ያለውን ክህሎትና እውቀት ለማዳበርና የፈጠራ ሃሳብን ለማበርከት ማገዙን ጠቁመዋል።

የ5 ሚሊየን ኢትዮጵያዊያን ኮደሮች ኢኒሼቲቭ ለዲጂታል ክህሎት ልማት አስተዋጽኦ እያደረገ እንደሚገኝም ጠቅሰዋል።
የዲጂታል መሰረተ ልማት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ እና የግሉ ዘርፍ ለዲጂታል ልማት የበኩሉን ሚና እንዲወጣ የሚያስችል ምህዳር መፈጠሩን ተናግረዋል።
ለሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ ፣ ሂሳብና ምህንድስና ትኩረት በመስጠት ከትምህርት ተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነውም ብለዋል።
የአፍሪካ ሮቦቲክስ ውድድር ፈጠራን የሚደግፉ ስራዎች የሚታዩበት እንደሆነና ሃሳብን በማልማትና በማሳደግ እንዲሁም ወደተግባር በመለወጥ ሀብትና የስራ እድል እንደሚፈጥር ጠቁመዋል።
የኢትዮ ሮቦቲክስ የማዕከሉ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰናክሬም መኮንን በበኩላቸው፤ ውድድሩ የተማሪዎችን የፕሮግራሚንግ፣ ዲዛይን፣ ምህንድስና እና ተዛማጅ ክህሎቶቻቸውን እንዲያሻሽሉ የሚያግዝ ነው ብለዋል።
የአፍሪካ ሮቦቲክስ ሻምፒዮንሺፕ ውድድር ለሦስት ቀናት የሚካሄድ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ የሚገኙ የመንግሥት፣ የግልና የዓለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ይሳተፋሉ።
ሆሳዕና ፤ ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦በሆሳእና፣ ወላይታ ሶዶና ቦንጋ ከተሞች በትንሳዔ በዓል ገበያ በቂ የምርትና የእርድ እንስሳት አቅርቦት መኖሩ ተመለከተ። ...
Apr 12, 2026
አዲስ አበባ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦የጉምሩክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የጉምሩክ አገልግሎት በሚያቀላጥፍ መልኩ እየተዘጋጀ መሆኑን በሕ...
Apr 9, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፦ የአፋር ሰመራ ሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ወደ ሥራ መግባቱ በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025