
አዲስ አበባ፤ የካቲት 27/2017(ኢዜአ)፦ጥራቱን የጠበቀ የቆዳ ምርቶችን ለዓለም ገበያ በማቅረብ ላይ ለሚገኙ ሶስት አምራች ፋብሪካዎች እውቅና ተሰጥቷል፡፡
እውቅናውን የኢትዮጵያ አምራቾች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት፣ የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት እና የአውሮፓ ሕብረት ናቸው በጋራ የሰጡት፡፡
በእውቅና መርሐ ግብሩ ኢትዮ ሌዘር ኢንዱስትሪ (ኤሊኮ) አዋሽ እና አቢሲኒያ የቆዳ ፋብሪካዎች የወርቅ ተሸላሚ ሲሆኑ ባቱ ደግሞ የብር ደረጃ ተሸላሚ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ አምራቾች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሚሊኬሳ ጃገማ በዚሁ ወቅት፤ ኢትዮጵያ በቆዳ ኢንዱስትሪው ዘርፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥራት ያለውና ተወዳደሪ የሆኑ ምርቶችን ለማቅረብ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እያከናወነች ነው።
ፋብሪካዎቹ በተለይም የምርት ጥራትን፣ የሰራተኛና የአካባቢ ደህንነትን በመጠበቅ እንዲሁም በአጠቃላይ አለም አቀፍ መስፈርቶችን በማሟላታቸው እውቅና ማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም፥ በቆዳ ሀብት ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት መንግስት ከሚሰራቸው ሰራዎች በተጨማሪ በሴክተሩ ያሉ የባለድርሻ አካላት ትብብር ሊጠናከር እንደሚገባ ተናግረዋል።
የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (ዩኒዶ) በቆዳ ዘርፍ ዘላቂ የስራ እድል ለመፍጠር የሚሰራ ኢኒሼቲቭ አስተዳደር አውሬሊያ ካላብሮ በበኩላቸው ዩኒዶ የቆዳው ዘርፍ ላይ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን ገልፀዋል።
የቆዳ ኢንዱስትሪውን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ የዘርፉን ማህበር ማጠናከርና የቆዳ ምርታማነትን በማሳደግ ዘላቂነቱን ማረጋገጥ እንደሚገባም ተናግረዋል።
አዲስ አበባ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦የጉምሩክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የጉምሩክ አገልግሎት በሚያቀላጥፍ መልኩ እየተዘጋጀ መሆኑን በሕ...
Apr 9, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፦ የአፋር ሰመራ ሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ወደ ሥራ መግባቱ በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025