
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፡-በሃዋሳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በ60 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የተለያዩ ሶላር ፓኔሎችን ለማምረት የገባው የጃፓኑ ቶዮ ሶላር ኩባንያ የማሽን ተከላ ስራዎችን በማጠናቀቅ የሙከራ ምርት ማምረት ጀምሯል።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር)፥ በልዩ የኢኮኖሚ ዞኑ የቶዮ ሶላር ኩባንያን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴን ጎብኝተዋል፡፡
ዋና ስራ አስፈጻሚው፥ ኩባንያው በሙሉ አቅሙ ወደ ምርት ሂደት እንዲገባ ኮርፖሬሸኑ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።
የኩባንያው የስራ ኃላፊዎች በበኩላቸው የግንባታ ስራውን ሙሉ ለሙሉ አጠናቆ መጋቢት አጋማሽ ላይ በሙሉ አቅሙ ወደ ምርት ሂደት እንደሚገባ ጠቁመዋል።
ኩባንያው በተያዘው በጀት ዓመት በሃዋሳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ስራ ለመጀመር ከኮርፖሬሽኑ ጋር ተፈራርሞ ወደ ስራ የገባ ሲሆን ምርቶቹንም ወደ መካከለኛው ምስራቅ ፤ ህንድ እና አሜሪካ እንደሚልክ አስታውቋል፡፡
ቶዮ ሶላር ኩባንያ በሃዋሳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ሶስት ሄክታር የለማ መሬት እና የማምረቻ ሼድ ተረክቦ ስራ ጀምሯል።
ኩባንያው ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ቬትናም ውስጥ የሶላር ፓናል ማምረቻ ፋብሪካ አለው።
ኩባንያው በሙሉ አቅሙ ወደ ምርት ሂደት ሲጋበ ከአንድ ሺህ በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ቋሚ የስራ እድልን እንደሚፈጥር የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመለክታል።
አዲስ አበባ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦የጉምሩክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የጉምሩክ አገልግሎት በሚያቀላጥፍ መልኩ እየተዘጋጀ መሆኑን በሕ...
Apr 9, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፦ የአፋር ሰመራ ሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ወደ ሥራ መግባቱ በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025