
ሽሬ እንዳስላሴ፤ የካቲት 10/2017(ኢዜአ)፦በትግራይ ህጋዊ ያልሆነ የማእድን ኃብት አመራረትና አጠቃቀምን ለመከላከል በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ ተገለጸ።
የትግራይ ማእድን ኃብት ለዘላቂ ልማት፣ ዕድሎችና ተግዳሮቶቹ በሚል መሪ ሀሳብ አክሱም ዩኒቨርሲቲ ያዘጋጀው አውደ ጥናት በሽሬ እንዳስላሴ ከተማ ተካሂዷል።

የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ገብረ እየሱስ ብርሃነ በአውደ ጥናቱ ላይ እንዳሉት በክልሉ እየተስተዋለ ያለውን የተዛባ የማአድን ኃብት አጠቃቀም በመቅረፍ በተገቢው መንገድ ጥቅም ላይ ለማዋል በቅንጅት መስራት ይገባል ።
ህጋዊ ባልሆነ መንገድና ኃላፊነት በጎደለው አሰራር እየተከናወነ ባለው የማእድን ኃብት አጠቃቀም የተፈጥሮ ሃብቱ ለአገር እድገት ከመዋል ይልቅ ከፍተኛ ምዝበራ እየደረሰበት ነው ብለዋል።
እንዲሁም በሚደረገው ህገ ወጥ ፍለጋ በሰውና በእንስሳት ላይ ችግር እያስከተለ መሆኑን ተናግረዋል ።
ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት መንግስት ከዩኒቨርሲቲዎች፣ ከምርምር ተቋማትና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ሊሰራ እንደሚገባም አስገንዝበዋል ።
በአውደ ጥናቱ ላይ በማእድን አጠቃቀም ዙሪያ በተለያዩ ምሁራን ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
አዲስ አበባ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦የጉምሩክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የጉምሩክ አገልግሎት በሚያቀላጥፍ መልኩ እየተዘጋጀ መሆኑን በሕ...
Apr 9, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፦ የአፋር ሰመራ ሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ወደ ሥራ መግባቱ በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀ...
Apr 1, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025