ቦንጋ፤ ሐምሌ 23/2017(ኢዜአ)፦የሌማት ትሩፋት መርሀ ግብር የምግብ ዋስትናቸውን ከማረጋገጥ ባለፈ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን እንዳሳደገው በካፋ ዞን የቦንጋ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።
የሌማት ትሩፋት መርሀ ግብር በቤተሰብና በሀገር ደረጃ በምግብ እራስን ለመቻል እየተደረገ ያለውን ጥረት ለማሳካት ከፍተኛ አበርክቶ አለው።
ይህም በዘርፉ የተሰማሩ ዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ከማሳደግ ባለፈ በገበያ የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር እያገዘ ይገኛል።
በሌማት ትሩፋት መርሀግብር የተሰማሩት የቦንጋ ከተማ ነዋሪዎች ለኢዜአ እንደገለጹት መርሀ ግብሩ የምግብ ዋስትናቸውን ከማረጋገጥ ባለፈ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን እያሳደገው መጥቷል።
ከከተማዋ ነዋሪዎች መካከል ወጣት ዋቅጅራ ግብጣም በተሰማራበት የሌማት ትሩፋት መርሀ ግብር 700 እንቁላል ጣይ ዶሮዎች በማርባት በቀን እስከ 600 እንቁላል ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ እያቀረበ መሆኑን ተናግሯል።
ስራውንም በቀጣይ ለማስፋት በወተት ልማት፣ በእንስሳት እርባታ እና ማደለብ ሥራ ላይ ለመሰማራት ማቀዱንም ገልጿል።
ዘርፉ የቤተሰብን የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ ትርፋማ ያደርጋል ያለው ወጣቱ ሌሎችም በስራው ላይ በመሰማራት ተጠቃሚ እንዲሆኑ መክሯል።
በዚሁ ከተማ የሚኖሩት የ68 ዓመት የእድሜ ባለፀጋው አቶ አወል አሊ በበኩላቸው የአንድ ቀን የዶሮ ጫጩቶችን በማሳደግ ለህብረተሰቡ ማሰራጨታቸውን ተናግረዋል።
ባለፉት ሰባት ወራት 3ሺህ የአንድ ቀን ጫጩቶችን ማሰራጨታቸውንና ለሦስተኛ ዙር 1ሺህ 500 ጫጩቶችን እያሳደጉ መሆናቸውን አክለዋል።
ወጣቶችም ይህን አርአያነት ያለው ተግባር በመከተል ከስራ ጠባቂነት ወጥተው ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን እንዲያሳድጉ ልምዳቸውን ማካፈላቸውን ገልጸዋል።
የሌማት ትሩፋት መርሀ ግብር በከተማው የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ትልቅ አስተዋፅኦ እያደረገ መሆኑን የገለፁት ደግሞ የቦንጋ ከተማ አስተዳደር ግብርና፣ አካባቢ ጥበቃና ህብረት ሥራ ልማት ጽህፈት ቤት የእርባታ ሥራ ሂደት አስተባባሪ ወይዘሮ አታለለች ለገሰ ናቸው።
በከተማው 19 የወተት፣ የዶሮና የዓሣ መንደሮችን በማደራጀት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
የሌማት ትሩፋት በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ጠቁመው፣ ኢንሼቲቩ በእያንዳንዱ ግለሰብ ቤት ተግባራዊ እንዲሆን ሰፊ ሥራ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025