የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

የእንስሳት ጤና እና ምግብ ደህንነት ላይ የተዘጋጀ ውይይት ዛሬ በአዲስ አበባ ይካሄዳል

Jul 31, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ሐምሌ 22/2017 (ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ እየተካሄደ የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምግብ ስርዓት ጉባኤ አካል የሆነው የእንስሳት ጤና እና ምግብ ደህንነት ላይ የተዘጋጀ የውይይት መድረክ ዛሬ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

የምግብ ስርዓት ጉባኤው በተጓዳኝ በርካታ የጎንዮሽ የውይይት መድረኮች በመካሄድ ላይ ናቸው።

ከነዚህም መካከል የእንስሳት ጤና ኢኒስቲትዩት ከዓለም አቀፉ አቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ(አይኤኢኤ) እና የዓለም የምግብ እና እርሻ ድርጅት(ፋኦ) በጋራ ያዘጋጁት ሁነት ይገኝበታል።


ሁነቱ የዓለም አቀፉ አቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ(አይኤኢኤ) የብሔራዊ እንስሳት ጤና ምርመራ ቤተ ሙከራዎች ኔትወርክ(ቬትላብ ኔትወርክ) እንስሳት እና የጀርባ አጥንት ካላቸው እንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉ ድንበር ተሻጋሪ በሽታዎች በመለየት እና በመከላከል እንዲሁም የምግብ ደህንነትን ለማሻሻል ያላቸው ሚና ውይይት እንደሚደረግበት ከኢኒስቲትዩቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ፣ቦትስዋና፣ ቱኒዚያ እና ኮትዲቭዋር የስኬት ተሞክሯቸውን ያቀርባሉ።

ሁነቱ የኒውክሌር ቴክኖሎጂዎችና ቀጣናዊ ትብብር የምርመራ አቅምን፣ የበሽታ ቅኝት እና የክትባት ጥራትን በማሻሻል ረገድ ያላቸው ሚና ይዳሰሳል።

የሴቶች ሁሉን አቀፍ ተሳትፎን ከግምት ያስገባ ምክክር እንደሆነም ተገልጿል።

ሳይንስን መሰረት ያደረጉ የቁም እንስሳት ጤና ስርዓቶች ያላቸው የጤና እና የኢኮኖሚ ጠቀሜታዎች እንዲሁም በአፍሪካና እስያ የማይበገር ስርዓተ ምግብ መገንባት የሚያስችሉ ዘላቂ የመፍትሔ ሀሳቦች እንደሚቀርቡም ተመድ አስታውቋል።

የግብርና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢኒስቲትዩት ከዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት(ዩኒዶ) ጋር በመተባበር ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር እና ከዘመናዊ ቴክኖሎጂ ጋር የተቆራኘ የምግብ ስርዓት ግንባታ የሚያስፈልግ ኢንቨስትመንትን ተደራሽ ማድረግ ላይ ያተኮረ ውይይት ትናንት ማድረጋቸው የሚታወስ ነው።

በ ተጨማሪም የጉባኤው ተሳታፊዎች የተግባር ቀን ተብሎ በተሰየመው የመጀመሪያ ቀን የጉባኤው ውሎ ኢትዮጵያ በስርዓተ ምግብ ሽግግር ያከናወነቻቸውን ውጤታማ ተግባራት ጎብኝተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.