ሀዋሳ፤ሐምሌ 22/2017 (ኢዜአ)፦የሀዋሳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን በበጀት ዓመቱ ወደ ውጭ ከላካቸው ምርቶች ከ45 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማስገኘቱን አስታወቀ።
የልዩ ኢኮኖሚ ዞኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ማቲዮስ አሸናፊ ለኢዜአ እንደገለጹት፥ የሀዋሳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ከዚህ ቀደም በጨርቃ ጨርቅ ምርቶች ላይ ትኩረት አድርጎ ሲሰራ መቆየቱን አስታውሰዋል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን መሆኑን ተከትሎ በተለያዩ ዘርፎች ለመሰማራት ፍላጎት ያላቸው ባለሀብቶች ወደልዩ ዞኑ ለመግባት ስምምነት እየፈረሙ መሆኑን ገልጸዋል።
በተለይ የምስራቅ እስያ ካምፓኒዎች በብዛት እየገቡ እንደሚገኙ ጠቁመው፣ከእነዚህም በዓለም አቀፍ ደረጃ በሶላር ምርት ዕውቅና ያላቸው እንደ ቶዮ ሶላር፣ ካናዳ ሶላር እና ኦርጂን ሶላር የመሳሰሉ ካምፓኒዎች ፋብሪካቸውን ተክለው ወደምርት ሂደት መግባታቸውን ተናግረዋል፡፡
ይህም ከፍተኛ የሆነ የቴክኖሎጂ ዕውቀት ሽግግር፣የሥራ ዕድል ፈጠራ እንዲሁም የወጪ ምርት መጠን እንዲጨምር እና ገቢም እንዲያድግ ማድረጉን ተናግረዋል።
የሀዋሳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን በበጀት ዓመቱ ወደ ተለያዩ ሀገራት ከላካቸው ምርቶች ከ45 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱንም አቶ ማቲዮስ አንስተዋል፡፡
ገቢው የተገኘው ወደ አውሮፓ፣ሰሜን አሜርካ፣ እስያና አፍርካ ውስጥ በሚገኙ 14 የገበያ መዳረሻዎች ከተላኩ ምርቶች መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በሀዋሳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ከዚህ ቀደም ሥራ ላይ ከነበሩ ኩባንያዎች በተጨማሪ የተለያዩ ኩባንያዎች ስምምነት ፈርመው ወደ ምርት ሂደት መግባታቸው ተገልጿል፡፡
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025