የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በተጠናቀቀው በጀት አመት መዲናዋን ስማርት ሲቲ ለማድረግ መሰረት የተጣለበት ነው

Jul 30, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 18/2017(ኢዜአ)፦በተጠናቀቀው በጀት አመት በተከናወኑ ስራዎች መዲናዋን ስማርት ሲቲ ለማድረግ የሚያስችል መሰረት መጣሉን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ገለጹ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን አሰመልክቶ የ2017 በጀት አመት የስራ አፈጻጸምና የ2018 ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ መግለጫ ተሰጥቷል።


በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ እንደተናገሩት በተጠናቀቀው በጀት አመት ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል።

በበጀት አመቱ የህዝብ አመኔታን ያተረፉ፣ የተሻለ አገልግሎት መስጠትና ተወዳዳሪ መሆን የሚችሉ ተቋማትን መፍጠር መቻሉን አስታውቀዋል።

የህብረተሰብ ተሳትፎን በተሻለ መልክ ከማሳደግ እንዲሁም በጽዳትና ደህንነት ሞዴል አፍሪካዊ ከተማ ከማድረግ አኳያ ውጤቶች መገኘታቸውን ገልጸዋል።

እንዲሁም የተሳለጠ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ማቅረብ የተቻለበት መሆኑንም አስታውቀዋል።

እንደ ዋና ስራ አስኪያጁ ገለጻ፤ በተጠናቀቀው በጀት አመት በተከናወኑ ስራዎች መዲናዋን ስማርት ሲቲ ለማድረግ የሚያስችል መሰረት የተጣለበት ነው።

የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ንጉሴ በበኩላቸው በበጀት አመቱ ወቅታዊ ሁነቶችን የመመዝገብ አቅም መጨመሩን አንስተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛሀኝ ደሲሳ፤ ቆሻሻን ወደ ሀብት ምንጭ ለመቀየርና የስራ እድል ፈጠራን ከማሳደግ አንጻርም ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ መብራት አገልግሎት አስተዳዳር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰብስቤ ሁሴን በበኩላቸው፤ ተቋሙ በአዲስ አበባ ለመንገድ መብራት መሰረተ ልማቶች ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

የመንገድ መብራት በመትከል እና የተበላሹ ፖሎችን በመጠገን ወደ ስራ እንዲገቡ በማድረግ ለህብረተሰቡ ቅሬታ ምላሽ መስጠቱን አንስተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽነር አህመድ መሀመድ እንደገለጹት፤ ተቋሙ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ስራ በመስራት ለሁሉም ጥሪ ምላሽ እየሰጠ ይገኛል።

ጥሪ ከተደረገ ጀምሮ የስራ እንቅስቃሴ ለመከታታል የሚያስችል ግልጽ አሰራር ለመፍጠር በቴክኖሎጂ የመደገፍ ስራ እየተሰራ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.