የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ከድሬዳዋ ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ተደርጓል- ከንቲባ ከድር ጁሃር

Jul 25, 2025

IDOPRESS

ድሬዳዋ፤ሐምሌ 17/2017(ኢዜአ)፦ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከድሬዳዋ ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ መደረጉን የአስተዳደሩ ከንቲባ ከድር ጁሃር ተናገሩ፤

ድሬዳዋ ከተለያዩ የዓለም ከተሞች ጋር የተፈራረመችው የእህትማማችነት ስምምነት ለድሬዳዋ ሁለንተናዊ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች እና ለማህበራዊ ልማት ወሳኝ አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑም ተገልጿል ።

ከንቲባ ከድር ጁሃር ዛሬ በተጀመረው የአስተዳደሩ ምክር ቤት 3ኛ የሥራ ዘመን 4ኛ ዓመት 10ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ የአስፈፃሚውን እና የማዘጋጃ ቤት ተቋማትን የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት አቅርበዋል።


ከንቲባ ከድር በሪፖርታቸው ላይ ፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የአገሪቱን የብልጽግና ጉዞ ስኬታማነት ለማረጋገጥ የሚያግዝ ህያው ፕሮጀክት መሆኑን ገልጸዋል።

ፕሮጀክቱ መንግስትና ህዝብ ከተቀናጁ የትኛውንም የልማት ፕሮጀክት ዳር ማድረስ እንደሚችሉ የተረጋገጠበት መሆኑንም አመልክተዋል።

ፕሮጀክቱ የዛሬው ትውልድ ለቀጣዩ ትውልድ ከፍታ የራሱን የልማት ጀግንነት ማህተም ያተመበት ታሪካዊ ክስተት ነው ሲሉም ከንቲባ ከድር ጠቅሰዋል።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለሕዳሴው ግድብ ከአስተዳደሩ ነዋሪ ከቦንድ ግዥ ከ5 ሚሊዮን 595 ሺህ ብር በላይ ድጋፍ መደረጉንም አንስተዋል።የቦንድ ሽያጩ በህዝባዊ ንቅናቄ ተጠናክሮ መቀጠሉንም በመግለፅ።

"የሕዳሴው ግድብ ግንባታ ከተጀመረበት ዓመት ጀምሮ እስከአሁን ድረስ በቦንድ ሽያጭና በስጦታ ከአስተዳደሩ ከ108 ሚሊዮን 123 ሺህ ብር በላይ ድጋፍ ተደርጓል" ሲሉም አስታውሰዋል።

በቀጣይ በአስተዳደሩ ነዋሪዎች፣ ተቋማት፣ ባለሃብቶችና ሌሎች የሚያደርጉት ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ከንቲባ ከድር ጁሃር ድሬዳዋ ከተለያዩ የዓለም ከተሞች ጋር የተፈራረመችው የእህትማማችነት ስምምነት ለድሬዳዋ ሁለንተናዊ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች እና ለማህበራዊ ልማት ወሳኝ አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑን አመላክተዋል።

በተጨማሪም በመላው ዓለም የሚኖሩ የድሬዳዋ ተወላጆች እና ወዳጆች ለከተማዋ ዕድገት እያበረከቱት ያለው አስተዋጽኦ እየጨመረ መምጣቱን ተናግረዋል።

ለአብነትም በፈረንሳይ የሚኖሩ የድሬዳዋ ተወላጆችና ወዳጆች ከ95 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የህክምና ቁሳቁሶች ለአስተዳደሩ መደገፋቸውን ጠቅሰዋል።

ዛሬ የተጀመረው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት 3ኛ የሥራ ዘመን 4ኛ ዓመት 10ኛ መደበኛ ጉባዔ እስከ ነገ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ እንደሚመክር ታውቋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.