የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በክልሉ በተለያዩ ዘርፎች የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማስቀጠል የክትትልና ድጋፍ ተግባራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን-የምክር ቤት አባላት

Jul 24, 2025

IDOPRESS

ታርጫ፣ ሐምሌ 16/2017 (ኢዜአ):-በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በተለያዩ ዘርፎች የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማስቀጠል የክትትልና ድጋፍ ተግባራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ የክልሉ ምክር ቤት አባላት ተናገሩ፡፡

የክልሉ ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ጉባኤውን በታርጫ ከተማ አካሄዷል፡፡


አባላቱ በሚያደርጉት ቅኝትና ክትትል በተጠናቀቀው በክልሉ በጀት ዓመቱ በኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች የተሻለ አፈጻጸም መኖሩን መመልከታቸውን ገልጸው ይህም በቀጣይ በተቀናጀ አግባብ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

አስተያየታቸውን የሰጡ የምክር ቤት አባላቱ እንዳሉት፤ በክልሉ በተለያዩ ዘርፎች የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማስቀጠል የክትትልና ድጋፍ ተግባራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን።

ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል ወይዘሮ እንግዳወርቅ ዶኖቾ፣ እንዳሉት በክልሉ በበጀት ዓመቱ የህዝብን ጥያቄ መሰረት ያደረጉ የልማት እንቅስቃሴዎች መከናወናቸውን ምልከታ ባደረጉበት ወቅት ማስተዋላቸውን ተናግረዋል።

ከመሰረተ ልማት አኳያ በተደጋጋሚ በምክር ቤቱ ሲነሱ የነበሩ ተጀምረው ያልተጠናቀቁና የህብረተሰቡ የቅሬታ ምንጭ ሆነው የቆዩ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ የተወሰደው የተቀናጀ እርምጃ ውጤታማ መሆኑንም እንዲሁ።


ህብረተሰቡንና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ የተከናወኑ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት ላይ የተሰሩ ስራዎች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ያነሱት ደግሞ ሌላኛው የምክር ቤቱ አባል መስፍን ወዳጆ (ዶ/ር) ናቸው።

የምክር ቤቱ አባል አቶ ተረፈ ሀብተማሪያም በበኩላቸው በክልሉ የሚከናወኑ የልማት ስራዎች የህዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ እንዲሆኑ ምክር ቤቱ የሚጠበቅበትን ለመወጣት እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።


የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻልና በጤናው ረገድ ቅድመ መከላከል ላይ የተከናወኑ ተግባራት ውጤት የታየባቸው መሆኑን ገልጸው የበለጠ ማጠናከር ይጠበቃል ብለዋል ።

በግብርናው ዘርፍ የተመዘገበው ውጤት ቀጣይነት እንዲኖረው በቴክኖሎጂ የማስደገፍ ስራ ትኩረት ሊጠሰው እንደሚገባ የገለፁት አባላቱ ፣ የስራ ዕድል ፈጠራና ትምህርት ለትውልድ ላይ የተጀመሩ ጥረቶች ሊጠናከሩ ይገባል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.