አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 3/2017(ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት የተካሄደው ሶስተኛው የአፍሪካ የሥራ ዕድል ፈጠራ ፎረም እርስ በእርስ ለመማማርና ምርቶቻቸውን ለማስተዋወቅ ምቹ እድል እንደፈጠረላቸው አፍሪካውያን ስራ ፈጣሪ ወጣቶች ተናገሩ።
ላለፉት ሶስት ቀናት በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው 3ኛው የአፍሪካ የሥራ ዕድል ፈጠራ ፎረም ትናንት ተጠናቋል።
ከፎረሙ በተጓዳኝ በተዘጋጀው ኤግዚቢሽን ላይ ምርቶቻቸውን ያቀረቡ አፍሪካውያን ስራ ፈጣሪ ወጣቶች ለኢዜአ እንዳሉት ፎረሙ ትስስርን ለመፍጠርና ምርቶቻቸውን በተሻለ መንገድ መስራት የሚችሉበት ግብዓት ያገኙበት ነው።
ከኡጋንዳ የመጣችው የኢማሮ ኢኖቬሽን መስራች ካይክራ ባርብራ እንዳለችው በግብርና ምርቶች ላይ እሴት በመጨመር ወደገበያ እያቀረበች ትገኛለች።
በኢትዮጵያ በተካሄደው የሶስተኛው አፍሪካ የስራ እድል ፈጠራ ፎረም መሳተፏ ትስስርን በመፍጠር የምርት ጥራትን ለማሻሻል እንደሚያስችላት ገልፃለች።
ከዚምባብዌ የመጣችው የማጅስቲክ አፍሪካ ዳይሬክተር ጌትሩድ ቻምባቲ በበኩሏ በግብርና ምርት ማቀነባበር ላይ ተሰማርታ ምርቶችን ለገበያ እያቀረበች መሆኑን ተናግራለች።
የአፍሪካ የሥራ ዕድል ፈጠራ ፎረም ከገበያ ትስስር ባለፈ እርስ በእርስ ለመማማር እድል የፈጠራና ምርቶችን ለማስተዋወቅ ያስቻላት መሆኑንም ገልፃለች።
ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑን የገለጹት ተሳታፊዎቹ፤ አገሪቱ በፈጣን እድገት ላይ መሆኗን መመልከታቸውንም ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ለወጣቶች ስራ እድል ፈጠራ ምቹ የሆኑ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን አስተውለናልም ብለዋል፡፡
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025