የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

‎የሀዋሳ ከተማን ልማት በማፋጠን ለህዝብ ጥያቄ ምላሽ መስጠት ላይ ትኩረት ተደርጓል - አስተዳደሩ

Jul 10, 2025

IDOPRESS

‎ሀዋሳ፤ ሐምሌ 2/2017(ኢዜአ)፦ በበጀት ዓመቱ የሀዋሳ ከተማን ልማት በማፋጠን ለህዝብ ጥያቄ ምላሽ መስጠት ላይ ትኩረትመደረጉን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ መኩሪያ መርሻዬ ገለጹ።

ከንቲባው የበጀት ዓመቱን የልማትና መልካም አስተዳደር ሥራዎች አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።

ከንቲባው በመግለጫቸው ‎የከተማው ህብረተሰብ የልማት ጥያቄ ከሆኑት መካከል በተለይም የመንገድ፣ የውሃ፣ መብራትና ሌሎች ስራዎችን ደረጃ በደረጃ ምላሽ ለመስጠት መሰራቱን ጠቅሰዋል።

በከተማዋ ለተከናወነው ከ207 ኪሎ ሜትር በላይ የመንገድ ከፈታ ስራ ህብረተሰቡ ቋሚ ንብረቶቹን በማንሳቱ ለስራው መቀላጠፍ አጋዥ እንደነበርም ገልጸዋል።

‎በከተማዋ ውበትና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ ጉልህ ሚና ያለው የ2 ነጥብ 2 ኪሎ ሜትር የመጀመሪያው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ሥራም ተጠናቆ ለአገልግሎት መብቃቱን አንስተዋል፡፡

ስራውን በማስቀጠል 5 ነጥብ 6 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሁለተኛው ምዕራፍ ኮሪደር ልማትም 60 በመቶው መጠናቀቁን አክለዋል።

‎የከተማዋን የንፁህ መጠጥ ውሃ እጥረት ለመፍታት በ260 ሚሊዮን ብር የፋራ-ሂጣታ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ‎

ከ100ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርገው ይህ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት አፈጻጸምም 75 በመቶ መድረሱን አብራርተዋል፡፡

በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በአገልግሎትና ሌሎች ዘርፎችም ለ18ሺህ 341 ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል ብለዋል፡፡

ለቱሪዝም ዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው በበጀት ዓመቱ ወደ ከተማዋ ከመጡ የውጭና የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች 861 ሚሊዮን ብር ገቢ መገኘቱንም ጠቅሰዋል፡፡

ከተማ አስተዳደሩ የህብረተሰቡን የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ የገቢ አቅምን ማሳደግ ላይ ትኩረት በመስጠቱ 4 ቢሊዮን 535 ሚሊዮን ብር መሰብሰብ እንደተቻለ አስረድተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.