የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በመንግስት እና የግል አጋርነት ሜጋ ፕሮጀክቶችን የመፈጸም ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል-ሚኒስትር አህመድ ሽዴ

Jul 4, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 26/2017(ኢዜአ)፦በመንግስት እና የግል አጋርነት ሜጋ ፕሮጀክቶችን የመፈጸም ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ገለጹ።

ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በመንግስትና የግል አጋርነት የሚከናወኑ 7 ፕሮጀክቶች ስምምነት በተፈረሙበት ወቅት ነው።


የተፈረሙ ስምምነቶች አራት የቤት ልማት፣ ሁለት የቱሪዝም መዳረሻዎችንና የጤና መሰረተ ልማት በመንግስትና የግል አጋርነት ማልማት የሚያስችሉ ናቸው ተብሏል።

ኦቪድ ግሩፕ፣ አይሲኢ ዲቨሎፕመንትና ኮንስትራክሽን ድርጅት በቤት ልማት ፕሮጀክት፣ ቦስተን ፓርትነርስና ሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በቱሪዝም መዳረሻ ልማት፣ በሴርባ ላንሴት አፍሪካ እና ዓለም አቀፍ ክሊኒካል ላብራቶሪስ ተግባራዊ የሚደረገው የተቀናጀ የዲያግኖስቲክ አገልግሎት ግንባታ ፕሮጀክት በድርጅቶቹ ሃላፊዎች እና በሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት አመራሮች ተፈርሟል።

የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ በፊርማ ስነስርዓቱ ወቅት እንዳሉት የተደረጉት ስምምነቶች በመንግስት ልዩ ትኩረት የተሰጣቸውን ፕሮጀክቶች በመንግስትና የግል አጋርነት ማከናወን የሚያስችሉ ናቸው።


በቀጣይም ሀገራዊ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን በግልና የመንግስት አጋርነት የመፈጸም ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

የተደረጉት ስምምነቶች የሀገር ውስጥ ባለሀብቶችን በማበረታታት ትልቅ ፋይዳ እንዳላቸው በመጠቆም ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.