የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

የክልሉ ጸጥታ ሀይል ሰላምን ከማስከበር ባሻገር የጋራ አሻራ ለሆነው የህዳሴ ግድብ ሲያደርግ የቆየው ድጋፍ የሚበረታታ ነው

Jul 4, 2025

IDOPRESS

አዳማ ፤ ሰኔ 26/2017(ኢዜአ)፡- የኦሮሚያ ክልል ጸጥታ ሀይል ሰላምን ከማስከበር ባሻገር የኢትዮጵያውያን የጋራ አሻራ ለሆነው ህዳሴ ግድብ ሲያደርግ የቆየው ድጋፍ አበረታች መሆኑን የክልሉ ምክትል ርዕስ መስተዳደር አወሉ አብዲ ገለጹ።

የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የተረከበውን የህዳሴ ግድብ ዋንጫ ለክልሉ ዞኖችና ከተሞች ፖሊስ መምሪያዎች አስረክቧል።


በስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙትየክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት አወሉ አብዲ እንደገለፁት፤ የክልሉ የጸጥታ ሀይል ሰላምን ለማረጋገጥ ውጤታማ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል።

የጸጥታ ሀይሉ ከመደበኛ የሰላም ማስጠበቅ ስራ ባሻገር ህዝቡን ተጠቃሚ በሚያደርጉ የልማት ስራዎችም የራሱን አሻራ እያሳረፈ ይገኛል ብለዋል።

በተለይም የጸጥታ ኃይሉ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሂደት የበኩሉን ሚና ሲወጣ መቆየቱን አስታውሰው፤ ዛሬም የህዳሴ ግድብ ዋንጫ የግድቡ ግንባታ መቋጫ ምዕራፍ ላይ ባለበት ጊዜ ወደ ክልሉ መምጣቱ ቀኑን ልዩ ያደርገዋል ነው ያሉት።


አሁንም ግድቡ እስከሚመረቅ ድረስ በየደረጃው ያለው የፀጥታ ኃይል፣ ባለሃብቶችና መላው የክልሉ ነዋሪዎች የነቃ ተሳትፎ በማድረግ የገቢ አሰባሰብ ሂደቱ ላይ እንዲሳተፉ አመልክተዋል።

በቀጣይም የክልሉ ነዋሪዎችየህዳሴው ግድብ በደለል እንዳይሞላና ረዥም አገልግሎት እንዲሰጥ በአካባቢ ጥበቃ፣ በተፋሰስ ልማት እና በችግኝ ተከላ የሚያደርጉትን ተሳትፎ እንዲያጠናክሩም አስገንዝበዋል።

የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌተናል ጄኔራል ዲሪባ መኮንን በበኩላቸው፤ የክልሉ ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታ ሃይሎች ጋር በመሆን የክልሉን ሰላም በማስጠበቅ ወሳኝ ሚና እየተጫወተ ይገኛል ብለዋል ።


የፀጥታ ኃይሉ የአካባቢውንና የክልሉን ሰላም አስተማማኝ ከማድረግ ባሻገር የህብረ ብሔራዊ አንድነትና የጋራ አሻራ የሆነው ህዳሴ ግድብ ከዳር እንዲደርስ በገቢ አሰባሰብ ሂደቱ የሚያደርገውን ተሳትፎ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

በዛሬው መርሃ ግብርም የህዳሴ ግድብ ዋንጫ በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አማካኝነት የሐረርጌ ክላስተር ፖሊስ መምሪያዎች ተረክበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ለተነሳላቸው ጥያቄ በሰጡት ማብራሪያ ''የሕዳሴ ግድብ ግንባታ አልቋል፣ ግድቡን እናስመርቃለን'' ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.