የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

<p>ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዓለም ባንክ ከምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ቀጣና ምክትል ፕሬዝዳንት ጋር ተወያዩ</p>

Feb 18, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ የካቲት 10/2017(ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዓለም ባንክ የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ቀጣናዊ ምክትል ፕሬዝዳንት ቪክቶሪያ ኳኳ (ዶ/ር) ጋር ተወያዩ።

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው በዓለም ባንክ የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ቀጠናዊ ምክትል ፕሬዝዳንት ከሆኑት ቪክቶሪያ ኳኳ (ዶ/ር) ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርገናል ሲሉ አስፍረዋል።


በሰው ተኮር ስራ፣ በምገባ መርሃ ግብር፣ በሴቶችና ወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ፈጣን ለውጦች መመዝገባቸውን ገልፀው በከተማ ንፅህና አጠባበቅና ፍሳሽ አወጋገድ እንዲሁም የትራፊክ መጨናነቅን ለመቀነስ የጀመርነው ዘመናዊ የትራፊክ ስርዓት ዝርጋታ ስራ የሚበረታታ በመሆኑ ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸውልናል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.