አዲስ አበባ፤የካቲት 10/2017(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የአፍሪካ ድምፅ ለመሆን እየሰራችው ያለው ስራ የሚደነቅ ነው ሲሉ የኢጋድ ስራ አስፈፃሚ ቃል አቀባይ ፓቲያንስ ኒያንግ ገለጹ።
በአዲስ አበባ በተካሄደው 38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን የኢጋድ ስራ አስፈፃሚ ቃል አቀባይ ፓቲያንስ ኒያንግ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትን ጎብኝተዋል።
በጉብኝታቸው ወቅት በተመለከቱት ጉዳይ አስተያየታቸውን የሰጡት ቃል አቀባዩዋ ኢዜአ አፍሪካን ያማከለ አካሄድን እየተከተለ በመሆኑ ምስጋና ይገባዋል ብለዋል።
የአፍሪካን አመለካከት በማስተዋወቅ እና በሚዲያ ዘርፍ ላይ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ለማምጣት እያደረገ ያለውን ጥረትም አድንቀዋል።
ኢዜአ አፍሪካ ላይ ያተኮረ የሚዲያ ተቋም ሆኖ የማገልገል ዓላማ ያለው ፐልስ ኦፍ አፍሪካ የተሰኘ አህጉር አቀፍ የሚዲያ መድረክ በማቋቋም ላይ ይገኛል።
ጉብኝታቸውን ተከትሎ ቃል አቀባዩዋ ኢትዮጵያ ፐልስ ኦፍ አፍሪካ በሚል የጀመረችው የዲጂታል ሚዲያ አማራጭ ለአፍሪካ ዲጂታል እድገት ጥሩ ምሳሌ እንደሚያደርጋት ተናግረዋል።
ፐልስ ኦፍ አፍሪካ የተሰኘው ዲጂታል ሚዲያም የአፍሪካን ታሪክ ለመንገር የበኩሉን አስተዋፅኦ እንደሚያበረክትም ገልጸዋል።
አፍሪካውያን በዓለም ዙሪያ እየተከሰተ ባለው የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፈጠራ ላይ የበለጠ ኢንቨስት እያደረጉ ነው፣ ፐልስ ኦፍ አፍሪካ እኛም ወደ ኋላ እንዳልቀረን ያመላክታል ብለዋል።
እንደ ቃል አቀባዩዋ ገለጻ፣ አፍሪካ የአህጉሪቱን እውነተኛ ታሪኮች ለመንገር በምታደርገው ጥረት ፐልስ ኦፍ አፍሪካ የራሱን ሚና እንደሚጫወት ገልጸው፣ እኛ የአፍሪካ መፍትሄዎች ከአፍሪካዊ መፍትሄዎች ይመነጫሉ እንላለን ነው ያሉት።
ለእርሳቸው አፍሪካ በራሷ እና በአካባቢያዊ እይታዎች ማስተዋወቅ ያለባት ውብ ታሪኮች ያሏት ውብ አህጉር ነች ሲሉም ገልጸዋል።
ኢጋድ ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና ከሌሎች የኢጋድ ክልል ሚዲያዎች ጋር በተለያዩ መንገዶች ተባብሮ ለመስራት ያለውን ቁርጠኝነት ገልፀዋል።
ከተቀሩት የሚዲያ ተቋማት ጋር በመተባበር በቀጣናው የሚሰሩ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችን አቅም ለመገንባት ኢጋድ እንደሚሰራም አረጋግጠዋል።
በዚህም ኢጋድ ቀደም ሲል ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ሲሰጥ የነበረውን የአቅም ግንባታ ስልጠና አጠናክሮ እንደሚቀጥልና ለጋዜጠኞች እውቅና የመስጠት ስራን እንደሚሰራም አረጋግጠዋል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025