የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

የለውጡ መንግስት የክልሉን የፖለቲካ ተሳትፎ ከማሳደግ ባለፈ በኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ዘርፎች አመርቂ ውጤት እንዲመዘገብ መሠረት ሆኗል

Apr 3, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አሶሳ፤ መጋቢት 24/2018 (ኢዜአ)፦ የለውጡ መንግስት የክልሉን የፖለቲካ ተሳትፎ ከማሳደግ ባለፈ በኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ዘርፎች አመርቂ ውጤት እንዲመዘገብ መሠረት መሆኑን በብልጽግና ፓርቲ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኢሳቅ አብዱልቃድር ተናገሩ።

መጋቢት 24 የለውጡ መንግስት የተሰጠውን ሀገራዊ ሀላፊነት በተመለከተ አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡት በብልጽግና ፓርቲ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢሳቅ አብዱልቃድር፤ ለውጡ የኢትዮጵያን የብልጽግና ጉዞ ጅማሮ ማብሰሪያ እንደነበር አስታውሰዋል።

ለውጡ በክልሎች መካከል የነበረውን የፖለቲካ ተሳትፎ የበላይነትና የበታችነት በማስቀረት ሁሉም በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ የሚወስኑበት አውድ መፍጠሩን ገልጸዋል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከለውጡ በፊት በነበረው የዳር ፖለቲካ ተሳትፎ በሀገር ጉዳይ ላይ የመወሰን አቅም እንዳልነበረው ጠቁመው የለውጡ መንግስት በፈጠረው አሳታፊ የፖለቲካ ስርዓት ተጠቃሚ መሆኑን አስታውቀዋል።

ከለውጡ መንግስት በፊት በነበረው ስርዓት ክልሉ የተፈጥሮ ሀብቱን በነፃነት መጠቀም እንዳይችል በመደረጉ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዳልነበረ አንስተዋል።

በአሁኑ ወቅት የለውጡ መንግስት በፈጠረው የብዝሃ ዘርፍ የኢኮኖሚ እሳቤ ክልሉ በግብርና፣ በማዕድን ልማት እና በሌሎች ዘርፎች ተጨባጭ ለውጥ ማምጣቱን ተናግረዋል።

የመደመር መንግስት ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ የወሰዳቸው የመፍትሄ አማራጮች በውጤት የታጀቡ መሆናቸውን የገለፁት አቶ ኢሳቅ፤ የተቋማት ግንባታም በማንኛውም ሁኔታ የማይበገሩ ሆነው እንዲቀረፁ መደረጉን አብራርተዋል።

ሀገራዊ ለውጡ ህብረብሔራዊ አንድነትንና የወል ትርክት ግንባታን በማጠናከር እንዲሁም አዳዲስ እሳቤዎችን በመተግበር የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ያረጋገጠ መሆኑን አክለዋል።

የመደመር መንግስት የተለያዩ የልማት ኢንሼቲቮችን በመተግበር ህብረተሰቡ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ከመሆን ባለፈ በአረንጓዴ አሻራና በስንዴ ልማት ለሌሎች ሀገራት ተሞክሮ የሚሆን ውጤት መመዝገቡን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ባለፉት 10 ወራት ከወጪ ንግድ 8 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6/2018(ኢዜአ)፦ባለፉት 10 ወራት ከወጪ ንግድ 8 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘት መቻሉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁ...

May 15, 2026

ረቂቅ አዋጁ የወጪና የገቢ ንግድን ለማሳለጥ የጎላ አስተዋፅኦ ይኖረዋል

አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፡-የጉምሩክ አዋጅ ረቂቅ ማሻሻያ የወጪና የገቢ ንግድን ለማሳለጥ የጎላ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው በህዝብ ተወካዮች ምክር ...

Apr 23, 2026

ኢትዮጵያ እና አይኤምኤፍ በኢኮኖሚው መስክ ትብብራቸውን ያጠናክራሉ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 9/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) በኢኮኖሚ ሪፎርም ትግበራ ዙሪያ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ለማጎ...

Apr 17, 2026

በጀጎል ግንብ ውስጥ የሚገነባው የ”ዳር ሀረር” የመልሶ ማልማት ፕሮጀክት ግንባታ ሊጀመር ነው

አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦ የሀረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በጀጎል አለም አቀፍ ቅርስ ውስጥ የሚገነባው የ''ዳር ሀረር'' መልሶ ማልማት ፕሮ...

Apr 12, 2026