🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሀገሪቱ የታየውን የዋጋ ግሽበት ቅናሽ ዘላቂ ለማድረግ የጀመረውን ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ ትግብራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ።
የባንኩ ገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ዛሬ ስድስተኛ መደበኛ ስብሰባውን አድርጓል።
ኮሚቴው ባወጣው መግለጫ፣ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት በየካቲት ወር መጨረሻ ወደ 9 ነጥብ 7 በመቶ ዝቅ ማለቱን ገልጿል።

ምንም እንኳን የሀገር ውስጥ የዋጋ ግሽበት እየቀነሰ ቢሆንም፣ በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ግጭት የነዳጅና የሸቀጦች ዋጋ መጨመር በኢኮኖሚው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሊኖረው እንደሚችል አመልክቷል።
በዚህም ምክንያት ኮሚቴው ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ (Tight Monetary Policy) መቀጠል እንዳለበት ወስኗል።
ብሔራዊ ባንኩ በሀገሪቱ እየታየ የመጣውን የዋጋ ግሽበት ቅናሽ አዝማሚያ ይበልጥ ለማረጋጋት፣ ባለፉት ወራት ሲተገብር የቆየውን ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ በቀጣይም አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

የባንኩ መነሻ ወለድ መጠን (NBR) ባለበት እንዲቀጥል እና ባንኮች ያላቸውን የቅሬታ ብድር (NPL) መጠን በመቀነስ የፋይናንስ ሥርዓቱ ጤናማነት እንዲጠበቅ አሳስቧል።
በተጨማሪም በመካከለኛው ምስራቅ ካለው ወቅታዊ ውጥረት ሊነሱ የሚችሉ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ስጋቶችን በንቃት መከታተል እንደሚያስፈልግም ነው የጠቆመው ኮሚቴው።

መንግስት የጀመረውን ጥንቃቄ የተሞላበት የበጀት አስተዳደር በማስቀጠል ከብሔራዊ ባንክ የሚወስደውን ቀጥተኛ ብድር እንዲያቆም እና የውጭ ምንዛሬ ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በምክረ-ሐሳቡ አመልክቷል።
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6/2018(ኢዜአ)፦ባለፉት 10 ወራት ከወጪ ንግድ 8 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘት መቻሉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁ...
May 15, 2026
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፡-የጉምሩክ አዋጅ ረቂቅ ማሻሻያ የወጪና የገቢ ንግድን ለማሳለጥ የጎላ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው በህዝብ ተወካዮች ምክር ...
Apr 23, 2026
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 9/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) በኢኮኖሚ ሪፎርም ትግበራ ዙሪያ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ለማጎ...
Apr 17, 2026
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦ የሀረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በጀጎል አለም አቀፍ ቅርስ ውስጥ የሚገነባው የ''ዳር ሀረር'' መልሶ ማልማት ፕሮ...
Apr 12, 2026