🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፦የአዲስ አበባን ዓለም አቀፍ የንግድና ኢንቨስትመንት ማዕከልነት የሚያጎለብት ዘመናዊ አሰራር ሥርዓት መፈጠሩን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በኢትዮጵያ እና በጣሊያን መካከል ያለውን የኢንቨስትመንት ፍሰት ወደ አዲስ ምዕራፍ አሸጋግሯል
የመጀመሪያው የኢትዮ-ጣሊያን የኮንስትራክሽን፣ የመሰረተ ልማትና የከተማ ልማት ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ፣ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር)፣ የጣሊያን የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ምክትል ሚኒስትር ማሪያ ትሪፖዲ፣ በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር ሴም ፋብሪዚ እና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።
በዚህ ወቅት የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ የመዲናዋ የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ የልማት ስኬቶች ዓለም አቀፍ ተወዳዳረሪነትን በማሳደግ ምቹ የኢንቨስትመንት መዳረሻነትን እያሳደገ ነው ብለዋል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ የተወሰዱ ተጨባጭ የአገልግሎት አሰጣጥ የሪፎርም እርምጃዎችም ኢትዮጵያን የንግድና ኢንቨስትመንት የስበት ማዕከል እያደረጋት እንደሚገኝ ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ የአዲስ መሶብ የዲጂታል የአንድ ማዕከልም አልሚ ባለሃብቶች የተሳለጠ የመንግስት አገልግሎት የሚያገኙበትን አስቻይ ምኅዳር መፍጠሩን ተናግረዋል።
ይህም የአዲስ አበባን ፈጣን ዕድገት በማሳለጥ ምቹ የንግድና ኢንቨስትመንት ካባቢን በመፍጠር የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ እያበረታታ መሆኑን አንስተዋል።
በንግድና ኢንቨስትመንት ለሚሰማሩ አልሚ ባለሃብቶች ድጋፍና ትብብር እየተደረገ እንደሚገኝም ጠቅሰዋል።

የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድ ኢትዮጵያን አፍሪካዊት የብልፅግና ተምሳሌት የሚያደርግ አመርቂ ውጤት እያስገኘ ነው ብለዋል።
ለአብነትም የሕዳሴ ግድብ ስኬት፣ አዲስ አበባን ጨምሮ ከ80 በላይ የከተሞች የኮሪደር ልማት ስኬቶች የኮንስትራክሽን ዘርፉን ፈጣን ዕድገት የሚያሳዩ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ፈጣን ዕድገትም በሃብት ፈጠራና አስተዳደር ተጨባጭ ለውጥ እንዲመጣ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
የኢትዮ-ጣሊያን የዲፕሎማሲ ወዳጅነት የጣሊያን ኩባንያዎች በግንባታ ግብዓት፣ ማሽነሪና መሰል የንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፍ የነቃ ተሳትፎ የሚያደርጉበትን ዕድል እንደፈጠረ አብራርተዋል።
የኢትዮ-ጣሊያን የኮንስትራክሽን፣ የመሰረተ ልማትና የከተማ ልማትፎረምም የሀገራቱን ትብብር ወደላቀ ምዕራፍ ለማሸጋገር ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6/2018(ኢዜአ)፦ባለፉት 10 ወራት ከወጪ ንግድ 8 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘት መቻሉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁ...
May 15, 2026
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፡-የጉምሩክ አዋጅ ረቂቅ ማሻሻያ የወጪና የገቢ ንግድን ለማሳለጥ የጎላ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው በህዝብ ተወካዮች ምክር ...
Apr 23, 2026
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 9/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) በኢኮኖሚ ሪፎርም ትግበራ ዙሪያ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ለማጎ...
Apr 17, 2026
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦ የሀረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በጀጎል አለም አቀፍ ቅርስ ውስጥ የሚገነባው የ''ዳር ሀረር'' መልሶ ማልማት ፕሮ...
Apr 12, 2026