🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 15/2018 (ኢዜአ)፦ ለዓመታት የተጓተቱ ፕሮጀክቶች ከጠፉበት እየተመለሱ፤ ከወደቁበት እየተነሡ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የጎንደርን የውኃ ጥም ይቆርጣል፤ የገበሬውን መሬት ያጠጣል፤ የአካባቢውን ምኅዳር ይለውጣል የተባለው የመገጭ የመጠጥ ውኃ ግድብ የደረሰበትን ደረጃ መጎብኘታቸውን አመልክተዋል።

ለዓመታት የተጓተቱ ፕሮጀክቶች ከጠፉበት እየተመለሱ፤ ከወደቁበት እየተነሡ ነው ብለዋል።
የሀገር ሀብት ፈሶባቸው መክነው እና ባክነው የቀሩ የኢትዮጵያ ፕሮጀክቶችን ከሞት እያስነሡ ማፋጠን የዚህ መንግሥት ልዩ መለያው መሆኑን ገልጸው የመገጭ ግድብ ደግሞ አስረጅ ምስክር እንደሆነ ተናግረዋል።
እሱ ራሱ የጀመራቸው ብቻ ሳይሆን ተጀምረው የውልደት ስብራት የገጠማቸው ፕሮጀክቶች በብልጽግና መንግሥት አዲስ እስትንፋስ እያገኙ ግንባታቸው እየተፋጠነ ይገኛል ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

“አቁሞ ያስቀርህ እንደ መገጭ ግድብ” የሚለው ቀርቶ የአካባቢው ሰው “ወድቀህ ተነሣ እንደ መገጭ ግድብ” ብሎ መተረት ጀምሯል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የብልጽግና መንግሥት ብሂል ያስቀይራል ሲሉ ተናግረዋል።
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6/2018(ኢዜአ)፦ባለፉት 10 ወራት ከወጪ ንግድ 8 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘት መቻሉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁ...
May 15, 2026
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፡-የጉምሩክ አዋጅ ረቂቅ ማሻሻያ የወጪና የገቢ ንግድን ለማሳለጥ የጎላ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው በህዝብ ተወካዮች ምክር ...
Apr 23, 2026
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 9/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) በኢኮኖሚ ሪፎርም ትግበራ ዙሪያ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ለማጎ...
Apr 17, 2026
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦ የሀረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በጀጎል አለም አቀፍ ቅርስ ውስጥ የሚገነባው የ''ዳር ሀረር'' መልሶ ማልማት ፕሮ...
Apr 12, 2026