🔇Unmute
አዲስ አበባ፤መጋቢት 10/2018 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ ተግባራዊ የተደረገው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ሀገሪቱን ምቹ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ከማድረግ ባለፈ፣ ኢኮኖሚዋን ወደ ላቀ ደረጃ እያሸጋገረ መሆኑን የአንሞል ፕሮዳክትስ ጀነራል ማናጀር ራጂቭ ሻርማ ገለጹ።
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ነጠላ የኢኮኖሚ አተያይን ወደ ብዝኅ ዘርፍ በማሸጋገር እመርታዊ ዕድገት እንዲመዘገብ እያስቻለ ነው
ጀነራል ማናጀሩ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤መንግስት የወሰዳቸው የማሻሻያ እርምጃዎች ለውጭ ባለሀብቶች የፈጠሩትን ምቹ ሁኔታ በዝርዝር አብራርተዋል።
በኢትዮጵያ የተፈጠረው ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታ ለህንድ ባለሀብቶች ሰፊ ዕድል መፍጠሩን ጠቅሰው፤ በተለይም የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በቅርቡ በኢትዮጵያ ያደረጉት ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት የኢንዱስትሪና የኢንቨስትመንት ትብብርን ወደ ላቀ ደረጃ አሸጋግሮታል ብለዋል።
ሀገሪቱ በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ቀደም ሲል ለውጭ ባለሀብቶች ዝግ የነበሩ የንግድ መስኮችን ክፍት ማድረጓ የኢንቨስትመንት አቅሟን በእጅጉ እንዳሳደገው ለአብነት ጠቅሰዋል።
ኢትዮጵያ ሳቢ የኢንቨስትመንት መዳረሻ እንድትሆን ያደረጓት ምክንያቶች በርካታ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡
በዚህም በኢትዮጵያ እየተገነቡ ያሉ ግዙፍ መሠረተ ልማቶች በተለይም በቅርቡ ግንባታው የተጀመረው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለንግድ እንቅስቃሴው ተጨማሪ ምቾት ይፈጥራል ብለዋል።
በሌላ መልኩ ሰፊ የሀገር ውስጥ ገበያ እና ከፍተኛ የምርትና አገልግሎት ፍላጎት መኖሩን ጠቁመው፤ ለኢንቨስትመንት ስራ ዝግጁ የሆነው ሰፊ ወጣት የሰው ኃይል ሌላው የሀገሪቱ ትልቅ አቅም መሆኑን አክለዋል፡፡
ባለሀብቶች ቪዛን፣ የሥራ ፈቃድንና ሌሎች አገልግሎቶችን በአንድ ማዕከል በተሳለጠ መልኩ እንዲያገኙ መደረጉ የመንግስትን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይም ገልጸዋል።
በውጭ ምንዛሬ ረገድ የተወሰደው እርምጃም ጤናማ የገበያ ሁኔታን በመፍጠር ኢንቨስተሮች እኩል የውድድር ሜዳ እንዲያገኙና ተወዳዳሪ አቅም እንዲገነቡ ማስቻሉንም ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ ኢንቨስት በማድረግ ልምድ ያላቸው ነባር ባለሀብቶች የሀገሪቱን እምቅ አቅም ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በማስተዋወቅ ረገድ ትልቅ ሚና ሊጫወቱ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6/2018(ኢዜአ)፦ባለፉት 10 ወራት ከወጪ ንግድ 8 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘት መቻሉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁ...
May 15, 2026
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፡-የጉምሩክ አዋጅ ረቂቅ ማሻሻያ የወጪና የገቢ ንግድን ለማሳለጥ የጎላ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው በህዝብ ተወካዮች ምክር ...
Apr 23, 2026
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 9/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) በኢኮኖሚ ሪፎርም ትግበራ ዙሪያ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ለማጎ...
Apr 17, 2026
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦ የሀረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በጀጎል አለም አቀፍ ቅርስ ውስጥ የሚገነባው የ''ዳር ሀረር'' መልሶ ማልማት ፕሮ...
Apr 12, 2026