የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ መጀመር የፋይናንስ ስርዓቱን የሚያሻሽልና አካታች ኢኮኖሚ ለመገንባት የሚያግዝ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

Jan 13, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ጥር 2/2017(ኢዜአ)፦ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ መጀመር የፋይናንስ ስርዓቱን የሚያሻሽልና አካታች ኢኮኖሚ ለመገንባት የሚያግዝ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያን ዛሬ በይፋ አስጀምረዋል፡፡

የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ የተለያዩ የንግድ አይነቶችን ታሳቢ በማድረግ ሶስት ልዩ ልዩ የገበያ አይነቶችን የሚያቀርብ ነው፡፡

እነርሱም የአክሲዮን ገበያ፣ የዕዳ ሰነድ ገበያ እና የአማራጭ ገበያ ናቸው፡፡


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ እንዳሉት፤ ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ስብራት ብሎም የዜጎችን ኑሮ ለማሻሻል ከተከናወኑ ስራዎች አንዱ ዲጂታላይዜሽን መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ዲጂታል ኢትዮጵያ አማካኝነትም የዲጂታል ፋይናንስ ስርዓትን ማስፋት መቻሉን ነው ያነሱት፡፡

በአሁኑ ወቅትም 51 ሚሊዮን ዜጎች የሞባይል ገንዘብ ተጠቃሚ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

በዲጂታል ባንኪንግ ዘርፍ የተመዘገበውን ስኬት በካፒታል ገበያ ስርዓት በመደገፍ ኢኮኖሚውን ይበልጥ ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባም ነው ያብራሩት፡፡

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በአፍሪካ ግዙፍ አየር መንገድ የሚያንቀሳቅስ፤ ግዙፍ የኃይል ግድብ እንዲሁም እንደ ኢትዮ-ቴሌኮም ያሉ ግዙፍ ኩባንያዎችን የገነባ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡


ይህ ግዙፍ ኢኮኖሚ ለሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ምቹ መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህም የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያም ውጤታማ እንደሚሆን አረጋግጠዋል፡፡

መንግስት ለውጤታማነቱ ጊዜ ወስዶ ሰፋፊ ጥናቶችን ማከናወኑን በመግለጽ፡፡

በሌላ መልኩ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ መጀመር ሃሳብ ኖሯቸው በገንዘብ እጥረት ምክንያት ስራ መጀመር ላልቻሉ ወጣቶችም ሃሳባቸውን አቅርበው ፋይናንስ እንዲያገኙ የሚያደርግ ስለመሆኑም አብራርተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.