የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

በጂንካ ከተማ በትንሳዔ በዓል ገበያ በቂ የእርድ እንስሳት ቀርበዋል

Apr 12, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ጂንካ፣ ሚያዝያ 3/2018 (ኢዜአ) ፡- በጂንካ ከተማ በትንሳዔ በዓል ገበያ በቂ የእርድ እንስሳት አቅርቦት መኖሩን ሸማቾች ተናገሩ።

እንደ ሸማቾቹ ገለጻ፤ ለበዓሉ የሚሆኑ የእርድ ሰንጋዎች፣ ፍየሎችና ዶሮዎች በስፋት ለገበያ ቀርበዋል።


በበዓል ገበያ ሲሸምቱ ያገኘናቸው የጂንካ ከተማ ነዋሪው አቶ በሃይሉ መንግስቱ እንደገለጹት፣ ለበዓሉ የሚሆኑ የተለያየ ደረጃ ያላቸው ሰንጋዎች በየዋጋ አማራጫቸው ቀርበዋል።


በተለይም በቂ የእርድ እንስሳት አቅርቦት በመኖሩ፣ ለሸማቹ በሚፈልገውና በአቅሙ ልክ መቅረብ መቻሉን ነው የተናገሩት።

በገበያው የእርድ እንስሳት አቅርቦት በበቂ ሁኔታ መኖሩን የገለጹት ደግሞ ሌላኛው ሸማች አቶ ሳሙኤል ቻለው ናቸው፡፡

በገበያው አቅርቦቱ በአማራጭ መቅረብ በመቻሉ ሁሉም አቅሙን ባገናዘበ መልኩ ሸምቶ በዓሉን እንዲያከብር አስቻይ ሁኔታ ስለመፈጠሩም አመልክተዋል።


በገበያው ላይ የሚታየውን የሰንጋ፣ የፍየልና የበግ እንዲሁም የዶሮ የዋጋ ሁኔታ በተመለከተ አስተያየታቸውን የሰጡት ሸማቾቹ፣ ከአቅርቦት አንጻር ችግር ባይኖርም የዋጋ ጭማሪ መታየቱን ጠቁመዋል።

የጂንካ ከተማ ንግድና ገበያ ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ሐዝሚ በበኩላቸው በገበያው የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይኖር እና ያለአግባብ ምርት ላይ ዋጋ እንዳይጨመር ግብረ ሃይል ተቋቁሞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡


በከተማው የግብርና ምርትም ሆነ የእርድ እንስሳት በቂ አቅርቦት በመኖሩ ሸማቹ የአቅሙን ያህል ገዝቶ በዓሉን ለማሳለፍ አስቻይ ሁኔታ አለ ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ቀጣናዊ ደኅንነትን በማስጠበቅ ለጋራ ብልፅግና ወሳኝ ነው

አዲስ አበባ፤መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ከሀገራዊ ጥቅም ባለፈ ለዓለም አቀፍ የንግድ መስመር ደህንነትን ...

Apr 8, 2026

የለውጥ ጉዟችንን ስንዘክር ያስመዘገብናቸውን ስኬቶች በማስቀጠል ነው

ዲላ ፤ መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦የለውጥ ዓመታቱን ጉዞ ስንዘክር ያስመዘገብናቸውን ስኬቶች በማስቀጠል መሆን አለበት ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ር...

Apr 8, 2026

የኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ስኬት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ተግባራዊ ውጤት ማሳያ ነው

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ንግድና ኢንቨስትመንት ስኬት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ተግባራዊ ውጤት ማሳያ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ...

Mar 27, 2026

የኢትዮጵያ የብዝኅ ኢኮኖሚ ልማት የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማሳደግ የኢንቨስትመንት ማዕከልነት እያረጋገጠ ነው

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የብዝኅ ኢኮኖሚ ልማት የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማሳደግ አህጉራዊ የኢንቨስትመንት ማዕከልነትን እያረጋገጠ ...

Mar 26, 2026