🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 28/2018 (ኢዜአ)፡- በተያዘው የበጀት ዓመት 200 ሺህ ቶን እሴት የተጨመረበት የድንጋይ ከሰል በማምረት ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ እየሠራ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የማዕድንና ኢነርጂ ልማት ኤጀንሲ አስታወቀ።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ጌታቸው ወልያብ (ዶ/ር) ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ በክልሉ የድንጋይ ከሰል ሀብት በስፋት መኖሩን አንስተዋል።

በአሁኑ ወቅትም በዳውሮ እና ኮንታ ዞኖች የድንጋይ ከሰል የማምረት ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም አስታውቀዋል።
በአጠቃላይ እንደ ክልል ያለውን የድንጋይ ከሰል መጠን በጥናት ለመለየት እየተሠራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።
በ2018 የበጀት ዓመት 200 ሺህ ቶን እሴት የተጨመረበት የድንጋይ ከሰል በማምረት በማዕከላዊ ገበያ በኩል ለሲሚንቶ ፋብሪካዎች ለማቅረብ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።

በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሦስት ወራት 82 ሺህ ቶን ማምረት መቻሉንም አስረድተዋል።
በማዕድን ዘርፉ በተያዘው የበጀት ዓመት እስካሁን ባለው ሂደት ለ1 ሺህ 499 ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩንም ተናግረዋል።
አዲስ አበባ፤መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ከሀገራዊ ጥቅም ባለፈ ለዓለም አቀፍ የንግድ መስመር ደህንነትን ...
Apr 8, 2026
ዲላ ፤ መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦የለውጥ ዓመታቱን ጉዞ ስንዘክር ያስመዘገብናቸውን ስኬቶች በማስቀጠል መሆን አለበት ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ር...
Apr 8, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ንግድና ኢንቨስትመንት ስኬት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ተግባራዊ ውጤት ማሳያ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ...
Mar 27, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የብዝኅ ኢኮኖሚ ልማት የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማሳደግ አህጉራዊ የኢንቨስትመንት ማዕከልነትን እያረጋገጠ ...
Mar 26, 2026