🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ህዳር 22/2018(ኢዜአ)፦ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ሥራዎች ከተሞችን ለኑሮና ለሥራ ምቹ፣ ውብና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ማስቻላቸውን የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ገለፀ።
የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ፈንታ ደጀን ለኢዜአ እንዳሉት መንግስት ከተሞችን ለዜጎች ኑሮ ምቹና ተስማሚ ከማድረግ ባለፈ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በልዩ ትኩረት እየሰራ ይገኛል።
በተለይም ከተሞችን ለህፃናት እና ለአረጋውያን ምቹ የማድረግ ስራ በስፋት በመከናወን ላይ ይገኛል ብለዋል።
በዚህም ከተሞች ያሏቸውን ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ሃብቶች በተገቢው መንገድ ጥቅም ላይ እንዲያውሉ የሚያስችሉ የልማት ስራዎች ተጠቃሽ መሆናቸውን አንስተዋል።
እንዲሁም አረንጓዴ ስፍራዎችን ለማስጠበቅ፣ ያለአግባብ ታጥረው የቆዩ መሬቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉ አስቻይ ሁኔታ መፍጠሩን ተናግረዋል።
በመሆኑም የዜጎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ ባሻገር ዘመናዊና ተወዳዳሪ ከተሞችን ለመገንባት የኮሪደር ልማቱ ትልቅ መነቃቃት መፍጠሩን አንስተዋል።
በአሁኑ ወቅት የኮሪደር ልማት ስራዎች በሁሉም ክልሎች ባሉ ከሰባ በላይ በሚሆኑ ከተሞች እየተከናወኑ መሆኑን ገልፀው በቀጣይ በሁሉም የሀገሪቱ ከተሞች ለማስፋት እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
የልማት ስራዎቹ የከተሞቹን ገጽታ የሚቀይሩና ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታቸው ከፍ ያለ መሆኑንም ሚኒስትር ዴኤታው ገልፀዋል።
የኮሪደር ልማቱ ከተሞችን ለኑሮና ለሥራ ምቹ ከባቢ እንዲኖራቸው እንዲሁም ውብና ማራኪ ገጽታ እንዲላበሱ ማድረጉን ጠቅሰው፣ ተወዳዳሪነታቸውም እያደገ መምጣቱን አንስተዋል።
ለአብነትም አዲስ አበባን ዘመናዊ፣ ውብና ተወዳዳሪ ከተማ በማድረግ ዓለም አቀፍ መድረኮችን ለማስተናገድ ግንባር ቀደም ተመራጭ እንድትሆን ማስቻሉን ገልጸዋል።
አዲስ አበባ፤መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ከሀገራዊ ጥቅም ባለፈ ለዓለም አቀፍ የንግድ መስመር ደህንነትን ...
Apr 8, 2026
ዲላ ፤ መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦የለውጥ ዓመታቱን ጉዞ ስንዘክር ያስመዘገብናቸውን ስኬቶች በማስቀጠል መሆን አለበት ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ር...
Apr 8, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ንግድና ኢንቨስትመንት ስኬት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ተግባራዊ ውጤት ማሳያ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ...
Mar 27, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የብዝኅ ኢኮኖሚ ልማት የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማሳደግ አህጉራዊ የኢንቨስትመንት ማዕከልነትን እያረጋገጠ ...
Mar 26, 2026