🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ሕዳር 16/2018 (ኢዜአ)፦ቡናን በጥሬው ብቻ ሳይሆን እሴት ጨምሮ በመላክ ለላቀ ስኬት መትጋት ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ለ2017 እቅድ አፈጻጸም መሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ባለድርሻ አካላት የእውቅና መርኃ ግብር አከናውኗል።

በመርኃ ግብሩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ ሚኒስትሮችና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በዚሁ ወቅት፤ከለውጡ በፊት የቡና ዘርፍ ተገቢውን ትኩረት ባለማግኘቱ እና በበርካታ ውስብስብ ችግሮች የተነሳ ለኢኮኖሚው የሚፈለገውን ገቢ ሳያመነጭ መቆየቱን አስታውሰዋል።

የመደመር መንግሥት ለአረንጓዴ ልማትና ለግብርና ዘርፍ በሰጠው ትኩረት ቡና አምራች አርሶ አደሮች የዕለት ፍጆታቸውን ከመሸፈን አልፈው ከፍተኛ ገቢ እያገኙ መሆኑን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ወደ ብልጽግና በምታደርገው ጉዞ የምትከተለው የዕድገት መርህ አረንጓዴ የዕድገት አቅጣጫን መሠረት ያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
የአረንጓዴ ልማቱ ካሻሻላቸው ዘርፎች አንዱ የቡና ልማት እና ምርታማነት መሆኑን ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ ቡናን ለዓለም ገበያ ማቅረብ ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ ፍጹም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በመጠንም ሆነ በገቢ ከፍተኛ ስኬት እያስመዘገበች መምጣቷን ጠቅሰዋል።

በ2017 በጀት ዓመት በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ 470 ሺህ ቶን ቡና በመላክ 2 ነጥብ 65 ቢሊየን ዶላር ገቢ ማግኘቷን አንስተዋል።
ይህ ውጤት በመደመር መንግሥት አመራር፣በባለሙያዎች ሙያዊ ክትትል እና ጥረት እንዲሁም በአርሶ አደሮች ትጋት የተገኘ መሆኑን ጠቁመዋል።
በተያዘው በጀት ዓመትም 600 ሺህ ቶን ቡና በመላክ ከ3 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ለማግኘት መታቀዱን ገልጸው፤ በቀጣይ ርብርባችን ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል ብለዋል።

በመንግስት በኩል የቡና ምርታማነትና ጥራት ለማሻሻል የሚያስችሉ ኢንሼቲቮች ተቀርጸው ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
ቡናን በጥሬው ብቻ ሳይሆን እሴት ጨምሮ በመላክ ለላቀ ስኬት መትጋት ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑንም አመላክተዋል።
ባለድርሻ አካላትም የተያዘውን እቅድ እንደሚያሳኩ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
አዲስ አበባ፤መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ከሀገራዊ ጥቅም ባለፈ ለዓለም አቀፍ የንግድ መስመር ደህንነትን ...
Apr 8, 2026
ዲላ ፤ መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦የለውጥ ዓመታቱን ጉዞ ስንዘክር ያስመዘገብናቸውን ስኬቶች በማስቀጠል መሆን አለበት ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ር...
Apr 8, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ንግድና ኢንቨስትመንት ስኬት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ተግባራዊ ውጤት ማሳያ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ...
Mar 27, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የብዝኅ ኢኮኖሚ ልማት የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማሳደግ አህጉራዊ የኢንቨስትመንት ማዕከልነትን እያረጋገጠ ...
Mar 26, 2026