🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 13/2018 (ኢዜአ)፡-ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ተወዳዳሪ የሆነ የባቡር አካዳሚ ልትገነባ ነው።
አካዳሚው የሚገነባው በቢሾፍቱ ከተማ ኪሎሌ ወረዳ ሲሆን፤ ግንባታው በ62 ሄክታር መሬት ላይ ያርፋል።

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) እና የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጅነር ሕሊና በላቸው፤ በቢሾፍቱ ከተማ ኪሎሌ ወረዳ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል።
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ከሁሉም አጎራባች ሀገሮች ጋር የሚያስተሳስሩ ዘመናዊ የባቡር መሠረተ ልማቶችን ከመዘርጋት ጎን ለጎን ኢንዱስትሪውን ከውጭ ጥገኝነት ለማላቀቅ የቴክኖሎጂ ሽግግር ስትራቴጂ ተቀርጾ ተግባራዊ እየተደረገ ነው።

ለባቡር ኢንዱስትሪው የሰለጠነ የሰው ሃይል በማፍራት ተተኪ ባለሙያዎችን የማሰልጠን ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ የሚገነባው የባቡር አካዳሚ ግንባታው ሲጠናቀቅ የኢንዱስትሪውን ተደራሽነት ለማስፋት እንደሚያግዝ ተናግረዋል።
ለአጎራባች አገራት ባለሙያዎች ስልጠናዎችን በመስጠት የውጭ ምንዛሬ ምንጭ ሆኖ እንደሚያገለግልም ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጅነር ሕሊና በላቸው በበኩላቸው፤ የባቡር ትራንስፖርት የወጪ እና ገቢ ምርቶችን እንቅስቃሴን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያሳልጥ ተናግረዋል።

አካዳሚው ተገንብቶ ሲጠናቀቅ ቀጣናውን በትምህርት ዲፕሎማሲ እንደሚያስተሳስር ተናግረዋል።
የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አለማየሁ አሰፋ እንደገለጹት፤ አካዳሚው ለከተማዋ በረከትና ተጨማሪ የቱሪስት መስህብ ሆኖ ያገለግላል።
በመሆኑም አካዳሚው በተቀመጠለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ ከተማ አስተዳደሩ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።
አዲስ አበባ፤መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ከሀገራዊ ጥቅም ባለፈ ለዓለም አቀፍ የንግድ መስመር ደህንነትን ...
Apr 8, 2026
ዲላ ፤ መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦የለውጥ ዓመታቱን ጉዞ ስንዘክር ያስመዘገብናቸውን ስኬቶች በማስቀጠል መሆን አለበት ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ር...
Apr 8, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ንግድና ኢንቨስትመንት ስኬት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ተግባራዊ ውጤት ማሳያ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ...
Mar 27, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የብዝኅ ኢኮኖሚ ልማት የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማሳደግ አህጉራዊ የኢንቨስትመንት ማዕከልነትን እያረጋገጠ ...
Mar 26, 2026